የሊቢያ ዉጊያ፤ ኔቶና የድርድር ጥያቄ

ሕዝባዊ ሠላማዊ አመፅ ወደ ጠመንጃ ዉጊያ ከተቀየረ ወዲሕ ግን ሕዝባዊዉ ድል በመጀመሪያ ፍጥነቱ አልቀጠለም።ኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊም የአመፁባቸዉን ሐይላት በሐል ከመደፍለቅ አላመነቱም።ታንክ፥ መድፍ፥ ተዋጊ ጄት፥ ሔሊኮብተር፥ የታጠቀዉ የቃዛፊ ታማኝ ጦር አማፂያኑ የሚቆጣጠሯቸዉን ከተሞች እያጠቃ ነዉ።