በዝቋላ ገዳም በቁጥጥር ሥር ውሏል የተባለው ቃጠሎ ዳግመኛ አገርሽቷል
ቃጠሎው የገዳሙን ዙሪያ ገባ እያካለለው ነው።
የቃጠሎው መንሥኤ “ከሰል አክሳዮች ናቸው” መባሉ አጠራጥሯል።
“ትናንት ምሽቱን
ነው ዳግመኛ የተቀሰቀሰው፤ የተጠበቀው የአየር እገዛ አልተደረገልንም፤ እሳቱ ዙሪያውን ይዞታል፤ በእሳቱ እየተከበብን፣ በጭሱ እየታፈንን
ቢሆንም ባፈር በቅጠሉ እየታገልን ነው፤ ወደ ጠበሉ ከገባ ግን አለን ለማለት አይቻልም፤ . .
. ገብረ መንፈስ ቅዱስ መቶ ዓመት ለጸለዩባት፣ ለደከሙባት ቅድስት ቦታ ምላሹ ይህ ነውን? እንዲያው ወሬ ብቻ ነን!!” /የገዳሙ
መነኰስ/
ዳሩ እሳት – መሀሉ እሳት!! በምሥራቅ እሳት – በመሀል እሳት – በሰሜን እሳት!!
ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊበን ዝቋላ ወረዳ አዱላላ ቀበሌ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ በሚገኘውና
የመንግሥት ይዞታ በሆነው ደን ምሥራቃዊ ገጽ ትናንት ቀትር ላይ ተነሥቶ ማምሻውን በቁጥጥር ሥር መዋሉ የተገለጸው ቃጠሎ ሌሊቱን አገርሽቶ ዙሪያ
ገባውን ከፍተኛ ጥፋት እያደረሰ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ከሚባለው ምሥራቃዊ ቦታ በምዕራብ አቅጣጫ የሴቶች ገዳም ወደሚገኝበት የኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያንና ወደ መሀል የገዳሙ ክልል
እየተዛመተ ነው፡፡
ጭስ እሳቱን ለማጥፋት የሚካሄደውን ጥረት በእጅጉ አዳጋች አድርጎታል፡፡ በቦታው በርከት ብሎ የሚታየው አስታ የተባለው
አጭር ዛፍ፣ የደረቀው ሣርና በበጋው ሙቀት የከቸረው መሬት/ አፈር እሳቱን በከፍተኛ ደረጃ በማቀጣጠል÷ በምሥራቅ አቅጣጫ በከባዱ ከሚነፍሰው ነፋስ ጋራ ተደማምሮ
ለእሳቱ በአጭር ጊዜ መዛመት አስተዋፅኦ ማድረጉን የገዳሙ መነኰሳት ተናግረዋል፡፡
የተጠበቀው እገዛ እንዳልደረሰላቸው አንድ የገዳሙ መነኮስ መግለጻቸው ተዘግቧል፡፡ እኚህ አባት እንዳስረዱት ቃጠሎው ከቁጥጥር ውጭ
ሆኖ ጠበል እየተባለ ወደሚጠራው ጫካ ከደረሰ የገዳሙን ጠቅላላ
ህልውና አጠያያቂ ያደርገዋል፡፡
እያስጨነቀን ነው፤ መሬቱ፣ ሣሩ፣ ቅጠሉ በጣም ደረቅ ነው፤ ይነዳል፤ ነፋስ አለ፤ ጭሱም ያፍናል፤ በዕድሜ የገፉ አባቶች ሳይቀሩ
በእሳት ተከበውም ቢሆን ባፈር በቅጠሉ ቢታገሉም ከአቅም በላይ ሆኗል፡፡”
ቦታ ምላሹ ይህ ነውን? እንዲያው ወሬ ብቻ ነን!!” ሲሉ የተሰማቸውን ብሶት ገልጸዋል፡፡
መምሪያ ምን ጥረት እየተደረገ እንዳለ በጎላ በተረዳ የተሰማ ነገር የለም፡፡
የዝቋላ ገዳም ዐፄ ገብረ መስቀል እና ቅዱስ ያሬድ ከነበሩበት አምስተኛው መ/ክ/ዘ ጀምሮ
የሚነገር ታሪክ ቢኖረውም በታወቀ መነሻ የቀናው ገድላቸውን በግብጽ ጀምረው በኢትዮጵያ በፈጸሙት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ
ቅዱስ አማካይነት በ1168 ዓ.ም እንደሆነ ይታመናል፡፡ ጻድቁ ሁለት ኪ.ሜ ርዝመት እና 60 ሜትር ጥልቀት ባለው የዝቋላ ሐይቅ
ውስጥ የቁልቁሊት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያና ለዓለም ሁሉ ለ100 ዓመታት እንደ ጸለዩ፣ በርእሰ ደብር ዝቋላም ለ262 ዓመታት
እንደኖሩ፣ በዚህም ወቅት ልዩ ልዩ የአጋንንትን ፈተና ድል መንሣታቸውንና ከጌታችን ዘንድ ቃል ኪዳን መቀበላቸውን በገድላቸው
ሰፍሮ ይገኛል፡፡
በ15ኛው መ/ክ/ዘ የነበረው ንጉሥ እንድርያስ (ሕዝበ ናኝ) በርእሰ
ደብር ዝቋላና በዙሪያው በመድኃኔዓለም፣ በእመቤታችን፣ በቅዱስ ገብርኤል፣ በቅዱስ ሚካኤል እና በጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ
ቅዱስ ስም አብያተ ክርስቲያን አሳንጧል፡፡
እኒህ አብያተ ክርስቲያን በግራኝ ወረራ ወቅት ጠፍተው ገዳሙ ጠፍ ሆኖ እስከ ንጉሥ ሣህለ
ሥላሴ እና ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ከቆየ በኋላ መተዳደሪያ መሬት (ጉልት)፣ አገልጋዮች ተሰጥተውታል፤ አብያተ
ክርስቲያኑም ዳግመኛ ታንፀዋል፡፡
በእሳተ ጎሞራ የተፈጠረ ሐይቅ (Crater Lake)
ተግኖ የሚገኝ ጥንታዊው የዝቋላ ገዳም በአምስቱ ዓመት የጠላት ወረራ ዘመን ከየካቲት 12፣ 1928
ዓ.ም ጭፍጨፋ በኋላ (ፋሽስት ኢጣልያ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ላይ
እንደፈጸመው ሁሉ) የአርበኞች መደራጃ ማእከል ነው በሚል ከባድ ጥፋት ቢያደርስበትም ፋሽስቱ በአየር ይሰንዝር የነበረውን
የቦምብ ድብደባ አንጥሮ የሚመልስ ታላላቅ ገቢረ ተኣምራት እንደተፈጸሙበት ይነገራል፡፡
ከ1989 ዓ.ም አንሥቶ ከርዳታ ጋራ በተያያዘ ወደ አካባቢው በገቡት ሉተራውያን ምክንያት
ገዳሙ ከሚደርስበት ሰው ሠራሽ ችግር በተጨማሪ በበጋ የውኃ እጥረት፣ በክረምት ደግሞ ከባድ ቁርና የመንገዱ አስቸጋሪነት
ተግዳሮቶቹ ናቸው፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን