ስለ ዝቋላ እሳት ጉዳይ – ምስጋና እና ስጋት
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 12/2004 ዓ.ም፤ ማርች 21/2012/ READ IN PDF)፦ ስጋቱ – ዛሬ አዳሩን ከምሽቱ 3፡00 ገደማ የቅዱሳን ከተማ በሚባለው ስፍራ ሲጤሱ የዋሉ የገመኑ (የተቃጠሉ) ጉቶዎችና ግንዶች ምሽቱን እሳት መቀስቀሳቸው ተሰምቷል፡፡ የእሳቱ መጠን ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ለጊዜው ማወቅ ባይቻልም÷ በየአቅጣጫው ሁኔታውን በንቃት እየቃኙ በነበሩት መናንያን በተሰማው ደወል በገዳሙ አዳራሽ የነበረው ምእመን እንዲጠራ ተደርጎ፣ በተራራው ላይ የመከላከሉን ተግባር በከፍተኛ ደረጃ ሲያግዙ ከነበሩት የፌዴራል ፖሊስ እና የመከላከያ ኀይሎች ጋራ የተቀሰቀሰውን እሳት ለማጥፋት እየተረባረቡ መሆኑ ተገልጾልናል፡፡
ትናንት ሌሊቱንና ዛሬ ውሎውን የቃጠሎው መዛመት ተግ ብሎ ከጋራው ግርጌ በኩል የሚጤሱ የጋሙ ጉቶዎች ጢስ ብቻ ነበር የሚታየው፡፡ ማምሻውን የተቀሰቀሰው እሳት በቃጠሎው ብዛት የገመኑት ግንዶችና ጉቶዎች የፈጠሩትን ፍሕም ጨርሶ ለማጥፋት በአየር የሚረጨው ኬሚካል በእጅጉ አስፈላጊ እንደ ሆነ ያለማቋረጥ እየቀረበ ያለውን ጥያቄ ትክክለኛነት የሚያስረግጥ ነው፡፡ በመሆኑም በጎ አድራጊ አካላት ለዚህ ተፈጻሚነት እንዲተባበሩ ተጠይቋል፡፡
ከዚህ ውጭ ያለው አማራጭ የነፍስ ወከፍ
የውኃ ርጭት ነው፡፡ ይሁንና ገዳሙ ከቀድሞም ባለበት የውኃ እጥረትና ከፍሕሙ መብዛት የተነሣ በቂ ውኃ ለማግኘት አይችልም፡፡ እስከ ኀሙስ ገበያ ድረስ ለመምጣት የቻለው ውኃም እየተቀዳ ቃጠሎውን ለማጥፋት ለተሰማሩት
ወገኖች ነው የተከፋፈለው፡፡ በመሆኑም በዚህም በኩል በጎ አድራጊ አካላት ውኃና ውኃ የሚያቀርቡ ተሽከርካሪዎችን በማቅረብ እንዲራዱ ተጠይቀዋል፡፡

እስከ አሁን – የገዳሙ መነኰሳት እስከ አሁን የተደረገውን ቃጠሎውን
የመከላከል ጥረት እንደሚከተለው ገልጸውታል፡- ‹‹በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በምእመኑ ብዛት እሳቱ ጠፍቷል፤ አሁን ባለበት ርቀት የሚበላውን ያህል በልቶ ስለጨረሰ ከዚህ
በኋላ ሊስፋፋ አይችልም፡፡
ሕዝበ ክርስቲያኑ፣ መከላከያው፣ ፖሊሱ፣ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ባለሞያዎች ወደ ገዳሙ መዳረሻ
በሆኑ መንገዶች አፈሩን እየቆፈሩ ጉድጓዶችን በማውጣት፤ አፈሩን፣ ቅጠሉንና ግንዱን በመከመር ቃጠሎው ወደ ጠበሉ እንዳይገባ አድርገውታል፡፡
በሆኑ መንገዶች አፈሩን እየቆፈሩ ጉድጓዶችን በማውጣት፤ አፈሩን፣ ቅጠሉንና ግንዱን በመከመር ቃጠሎው ወደ ጠበሉ እንዳይገባ አድርገውታል፡፡
አሁን የቃጠሎው ስጋት ያለው ጢሱ በሚታይበት ተራራ ግርጌ፣ በአዱላላ በኩል ጊዳ መሥመር እየተባለ
በሚታወቀው አቅጣጫ ነው፡፡ ሌሊት መናንያን ሁኔታውን በንቃት ይጠብቃሉ፡፡ የሚያሰጋ ከሆነ ደወል ይደውላሉ፡፡››
በሚታወቀው አቅጣጫ ነው፡፡ ሌሊት መናንያን ሁኔታውን በንቃት ይጠብቃሉ፡፡ የሚያሰጋ ከሆነ ደወል ይደውላሉ፡፡››
የገዳማውያኑ ምስጋና – ‹‹ለቦታው ተቆርቋሪ ከሆነው ወገን የቀረ ሰው የለም፡፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪው፣ የከተማው ወጣት፣ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች፣ ፖሊሱ፣ መከላከያው በአጠቃላይ ሕዝበ ክርስቲያኑ እዚሁ ነው
ያለው፡፡ በተለይ ወጣቱ ለቦታው ታላቅ ባለውለታ ነው፡፡ ሃይላንዳቸውን ብቻ ይዘው ተራራውን ወጥተው ከዚህ መድረሳቸው ብቻ ለእኛ
አለኝታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሐሳባቸውን ያስፈጽምላቸው፡፡ ውለታቸው በሰው ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡ ቦታውን ታድገውታል፡፡››
ያለው፡፡ በተለይ ወጣቱ ለቦታው ታላቅ ባለውለታ ነው፡፡ ሃይላንዳቸውን ብቻ ይዘው ተራራውን ወጥተው ከዚህ መድረሳቸው ብቻ ለእኛ
አለኝታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሐሳባቸውን ያስፈጽምላቸው፡፡ ውለታቸው በሰው ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡ ቦታውን ታድገውታል፡፡››
ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን