እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

Hon. Maître Artiste World Laureate Afewerk እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የዓለማችን፣ የኢትዮጵያና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ባለውለታ ናቸው…!!

ፍቅር ለይኩን [email protected]  

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ በ80 ዓመታቸው ማክሰኞ ማታ በጭጓራ ካንሰር ምክንያት ከዚህም ዓለም በሞት መለየታቸውን የሰማሁት በድንጋጤና በሐዘን ውስጥ ሆኜ ነበር። በቅርብ ጊዜያት ውስጥ በኢትዮጵያ ስነ ጹሑፍ ውስጥ እጅግ ትልቅና ልዩ ስፍራ ያላቸውን ሰዎችን አጥተናል፤ ዛሬ ደግሞ በስነ ጥበብ ሀገራቸውን በዓለም መድረክ ያስጠሩትን ታላቅና ዓለማቀፋዊ ሰው ኢትዮጵያ ተነጥቃለች።