የቴዲ አፍሮ "ጥቁር ሰው" ሙዚቃ
ዘነበ በቀለ
ምንም እንኳ የባህል ሙዚቃ በዋናነት መለኪያው ሀገራዊ የግንዛቤ ስልት ቢሆንም አንድን ሙዚቃ ለመገምገም በርካታ መለኪያዎችን ማስቀመጥ የሚያስፈልገው መሆኑ ግን ሀቅ ነው። በዚህም ምክንያት የቴዲን ሙዚቃ ስንገመግም መለኪያዎቻችንን በግልፅ ማስቀመጥ ግዴታ ነው። እንዲያው በደፈናው ደስ ይለኛል፣ አይለኝም፣ ብሎ መደምደም ይቻል ይሆናል፣ ነገር ግን እንደመገምገሚያ መሳሪያ ተደርጎ ሊወሰድና ወደ ትክክለኛም ግንዛቤ ሊመራ ይችላል ብሎ መገመት ስህተት ነው።