ቴዎድሮስ ካሳሁን ሲያዜም ኢትዮጵያ ትከበራለች (ዳኛቸው ቢያድግልኝ)

ዳኛቸው ቢያድግልኝ

አበሻ አንገቱን በሀዘን በሚደፋበት ወቅት ብቅ የሚሉ ፈርጦች አሉ፣ እንባችንን አብሰን ሀዘናችንን ተወት አድርገን ቀና እንድል የሚያደርጉን። ከትንሳዔው በዐል ጋር የሞራል ትንሳዔ የሚሰጥ ውብ ዘፈን ከጥግ አስከ ጥግ ድረስ ተሰማ። ብላቴናው ጥበብ ከላይ ይፈስለታል።