ወገኖቻችንን ለማስፈታት የተጠራ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በጄኔቭ

ወያኔ ኢህአዴግ : — · ዋልድባ ገዳምን ጨምሮ በሁሉም የእምነት ተቋማት ላይ እያካሄደ ያለውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ፣ · የሽብርተኝነት ታርጋ እየለጠፈ በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚያካሄደውን አፈናና የመብት ረገጣ በመቃወም ፣ · የዜጎችን ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት በመገደብ በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን መፈናቀል በመቃወም ፣ · በኢንቨስትመንት ስም በውጭ ባለሀብቶች አማካይነት እየተካሄደ ያለውን የመሬት ቅርምትና የዜጎች ከቀያቸው መፈናቀል በመቃወም ፣ · መምህራን ያቀረቡትን የመብት ጥያቄ በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ ጥያቄውን ለማዳፈን እየሄደበት ያለውን መንገድ በመቃወም ፣ · በአጠቃላይ ሐገራችን ኢትዮጵያ አሁን ለምትገኝበት አስከፊና አሳዛኝ ሁኔታ (የስብዓዊ መብት ጥሰት፣ ድህነት፣ በሽታና ድንቁርና ) የዳረጋትን ብልሹ፣ ጨቛኝና አምባገነን የአገዛዝ ስርዓት በመቃወም

እሮብ 25 አፕሪል 2012 ከ13:00 ሰዓት ጀምሮ በጄኔቭ የተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል:: እርስዎም በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተገኝተው ድምፅዎን እንዲያሰሙ ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን::
የሰልፉ አስተባባሪዎች