“ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት አልስማማም”
(ኤፍሬም እሸቴ – በግል)
ማክሰኞ ሚያዚያ 9/2004 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ እንደተለመደው የምክር ቤቱ ክቡራን አባላት በንባብ ላቀረቡላቸው ጥያቄዎቻቸው መልስ ሲሰጡ ተከታትያለኹ። ከጥያቄዎቹ አንዱ ወቅታዊው የሙስሊሞች ጉዳይ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው “መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ አልገባም” የሚለውን በሰፊው ሲያብራሩ ቆዩ።