ቱኒዚያውያን ተገላገሉ፤ ግብጾችም….እኛስ? በሲሳይ አጌና

ቬጋስን ጎብኝቶ፣ ውብ ህንጻዎቿን አይቶ፣ በማራኪ ትእይንቷ ውስጥ አልፎ ስለዚያ ለመጻፍ አለመቻል አለመታደል ነው። እንደኛ ላለው ሀገሩ በጣእር ላይ ላለችበት ከቬጋስ እንጻዎች በላይ ክፋታቸው የተከመረ ገዥዎች አሉብንና በሲዘር ፓላዝ፣ በፕላኔት ሆሊውድ፣ በኤም.ጂ.ኤም ግራንድ፣ በቢላጆ… ወዘተ ካዚኖ ሆቴሎች ስለሚታየው ትንግርት እና ትእይንት መቼ የምናወራበት ጊዜ ሆነ።