የቴዲ አፍሮ አልበም ሽያጭ ሬከርድ አስመዘገበ

ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ የተለቀቀው የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ‹‹ጥቁር ሰው›› አልበም በ300 ሺሕ ሲዲና በ120 ሺሕ ካሴት ሽያጭ፣ በአጠቃላይ ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ አሥር ሚሊዮን ብር ገደማ በማስገባት፣ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ኢንዱስትሪ ታሪክ አዲስ ሬከርድ ማስመዝገቡ ታወቀ፡፡