በሐረር ከተማ የሸዋበር ባለይዞታዎችና የክልሉ መንግሥት ሊግባቡ አልቻሉም

‹‹የታገዱት ብጥብጥና ሁከት ለማስነሳት ጥረት ሲያደርጉ በመገኘታቸው ነው››
የክልሉ መንግሥት
– በቃጠሎው የወደመው ንብረት እስከ አራት ቢሊዮን ብር ተገምቷል

በታምሩ ጽጌ እና በዘካሪያስ ስንታየሁ

በሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሐረር ከተማ ውስጥ ሸዋበር አካባቢ ጥር 4 ቀን 2003 ዓ.ም. ባልታወቀ ምክንያት በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ንብረታቸውን ላጡ ነጋዴዎች ዕርዳታ ለማሰባሰብና ዋና የገበያ ማዕከል እስከሚገነባ ድረስ ይሰጣል በተባለ ጊዜያዊ የገበያ ቦታ ምክንያት፣ ከክልሉ አስተዳደር ጋር ያልተግባቡ ሦስት ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ማኅበራት ከየካቲት 15 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ መታገዳቸው ታወቀ፡፡