ድንገተኛው የሥጋ ዋጋ ንረት ሸማቾችን አስደንግጧል

– የኮንትሮባንድ ንግድ መድራቱ በምክንያትነት ቀርቧል

ከትንሳዔ በዓል ጀምሮ ባልታሰበ ሁኔታ የሥጋ ዋጋ በመናሩ የተነሳ መግዛት እንዳቃታቸውና እንዳስደነገጣቸው ሸማቾች ገለጹ፡፡ ድንገተኛ ነው በተባለው ጭማሪ ከሥጋ ጋር መራራቅ እንደተፈጠረባቸው ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡