የኤርትራውያንን ንብረቶች ከወኪሎቻቸው የገዙ ኢትዮጵያውያን ጫና እየተደረገብን ነው አሉ
በታምሩ ጽጌ
የኤርትራ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ፈጽሞት በነበረው ወረራ ምክንያት ለብሔራዊ ደኅንነት ስጋት ይሆናሉ ተብለው ከአገር እንዲወጡ የተደረጉ ኤርትራውያንን ንብረት ከወኪሎቻቸው ላይ የገዙ ኢትዮጵያውያን፣ ንብረቶቹን እንዲመልሱ በተለያዩ መንገዶች ግፊትና ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡