የቴዲ አፍሮን አልበም ያልገዛሁባቸው 5 ምክንያቶች
ባለፈው ሳምንት የቴዲ አፍሮን አልበም እንድንገዛ የሚያስገድዱንን 5 ምክንያቶች አንብቤ ነበር፤ አላሳመኑኝም እንጂ! ስለዚህ አልገዛሁም፡፡ ባልገዛም አዳምጬዋለሁ፡፡ በርግጥ ሳይወጣ በፊት ላለመግዛት መወሰኔ በራሱ፣ ከወጣ በኋላ ለምን አልገዛሁትም ብዬ የምናገረው ነገር ሰሚን ላይማርክ ይችላል ግን ምንአገባኝ፡፡ ግን ምናልባት ‹ገንዘብ ቸግሮት የቴዲን አልበም አልገዛም› ብለው የሚያሙኝን ሰዎች ዝም ለማሰኘት ምክንያቴን እደረድራለሁ፡፡ (በነገራችን ላይ ትላንት ከኢትዮፒካሊንክ እንደሰማሁት÷ ያቺ እንኳን የፕሬዚደንት ግርማ ወልደጊዮርገስን የሕይወት ታሪክ በዶኩመንተሪ እሰራለሁ ስትል የነበረችው አምለሰት ሙጪ ስንት ሳዱላዎች የተጋደሉለትን ቴዲን በእጇ አደረገችው ማለት ነው በቃ?)
5. የአማርኛ አልበም መሆኑን አላወቅኩም ነበር
አልበሙ የአማርኛ መሆኑን ያወቅኩት ከሰማሁት በኋላ ነው፡፡ ምክንያቱም በየቦታው የተለጣጠፉት ግባብዲያ ማስታወቂያዎች በሙሉ ‹Tikur Sew, Get ready, A feast for soul, Teddy Afro ምናምን ይሉና፤ ለሳቅ ለጫወታ ማን እንደ ሜታ!› ይላሉ፡፡ እኔ የመሰለኝ ታዲያ ‹ትኩር ሰው› የሚባል የእንግሊዝኛን አልበም በኢትዮጵያዊ ቢራ አጣጥሙ የተባለ ነበር፤ እንግሊዝኛ እውቀቴ ውሱን ስለሆነ ያገሬን ዘለሰኛ ብሰማ ይሻለኛል ብዬ ነበር፡፡ እሺ! ቀልዴን ነው፡፡ የእንግሊዝኛ አልመሰለኝም፤ ነገር ግን ራሱን እንደኢትዮጵያዊ አርአያነት የሚቆጥረው ቴዲ አልበም ማስታወቂያ በእንግሊዝኛ ብቻ ሲሰራ ማኔጀሩ እና ፕሮሞተሩ አገሩ ኢትዮጵያ እንደሆነ ቢጠፋቸው እንኳን እሱን አላማከሩትም ነበር? አላምንም!
4. የነጠላ ዜማዎቹ ግጥምና ዜማ originality ስላነሳቸው
የቴዲ አፍሮ ዘፈኖች በግጥምም፣ በዜማም ስሜት ይኮረኩሩ እንደነበር የታወቀ ነው፡፡ ሆኖም ባሁኑ ሲለቃቸው የነበሩት ዜማዎች አንዴ ከኤርትራ፣ አንዴ ከሩቅ ምናምን የተቀነጫጨቡ መሆናቸውን ስንሰማ ታዝበናል፡፡ አንድ ግጥሙም ከማኅልዬ ማኅልዬ ዘ ሰለሞን ቃላቶች የተገጣጠሙ መሆናቸው አደናግሮኝ ነበር፡፡ እንዲያውም አንድ ጓደኛዬ ‹‹በቃ ቴዲ የሚችለው ግጥም ነው፤ ዜማ ከየትም፣ ከየትም ትንሽ እየቀባባ…›› ያለውን ለማመን ተቃርቤያለሁ፡፡ የሚያሳዝነው ግን አልበሙን ካደመጥኩ በኋላ ‹ያ አስደናቂው፣ አወዛጋቢው፣ አዲስ ምልከታ አጫሪው የቴዲ አፍሮ የግጥም ችሎታ የት ገባ?› አሰኝቶኛል፡፡
3. አልበሙ ስለወረደብኝ!
እዚህችጋ የቴዲ አድናቂ ብቻ ለመሆን የተፈጠሩ የሚመስሉት አድናቂዎቹ÷ የቴዲ ዘፈኖች አድማጭ ያስፈልገዋል ሊሉኝ ይችላሉ፡፡ ዘፈኖቹን ሦስት፣ አራቴ ሰማሁዋቸው፡፡ ተመልሶ ችክ ባሉ ችክችካዎች ሊያተክረን መሆኑን ሳስበው አሳዘነኝ፡፡ አልበሙን አውሶ ያስቀዳኝ ጓደኛዬም ቴዲን ከጠበቅኩበት በታች ሳገኘው ‹‹ሆዴ ባባ፣ ተናነቀኝ እምባ›› እንጂ አላነደደኝም አለኝ፡፡ ምናልባት ኃይል የሚለው ዘፈን ላይ ያለው ከኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የተወሰደ ዜማ በሬጌ ስልት ሲሰማ የሚሰጠው ጣዕም ወጣ ያለና የሚያረካ ሊባል ይችል ይሆናል፡፡ ከዚያ በተረፈ እነ ጃ ያስተሰርያልን፣ እነ ካብ ዳኅላክን፣ እነ ሼመንደፈርን በሰማሁበት ጆሮዬ እና እሱም በዘፈነበት አፉ አሁን የዘፈናቸው ለኛም ከሚገባን በታች፣ ለእርሱም ከሚችለው በላይ ሳይሆን አይቀርም፤ ትንሽ ይደብራል፡፡
2. ውድ ነው፤ (ዋጋው!)
30 ብር ለአንድ አልበም?! በዚህ ዘመን ቴክኖሎጂ፣ በአምስት መቶ ሺኅ ቅጂዎች የሚዘጋጅ አንድ ሲዲ ከነሽፋን ማሸጊያው ጭምር የሚፈጀው ዋጋ 5 ብር አይሞላም፡፡ ታዲያ የእርሱ አልበም ምን ስለሆነ ነው 30 ብር የሚሸጠው? በየትኛውም ቴክኖሎጂ ቢሰራ ኮፒ ማድረግ እንደሚቻል ስለማውቅ፣ ኮፒ አድርጌ ተጠቅሜያለሁ፡፡ በበኩሌ አልበሙ 11 ዘፈኖች ስላሉት፣ በ11 ብር ቢሸጥ ኖሮ የመጀመሪያውን (original) ቅጂ እገዛ ነበር፡፡ ይህችኛዋ አመፃ በቴዲ ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም አርቲስቶች ላይ ነው - አዎ! ኦሪጅናል የሚባለውን አልገዛም፡፡ ምክንያቱም ተመሳሳይ ጥራት ያለውን ቅጂ፣ በነፃ ወይም ግፋ ቢል በ5 ብር አገኛለሁ፡፡ አሥር ብር የምትሸጡ ከሆነ ‹‹ለጥበቡ እድገት›› ስል እተባበራችኋለሁ፡፡
1. ይህንን መንግስት እና ይህንን ኑሮ አላማረረም (I don’t want art for the sake of art)
‹እንዴ ቴዲ እኮ ዘፋኝ ነው?› ካላችሁ፣ እንዴ እስክንድርም እኮ ጋዜጠኛ ነው እላችኋለሁ፤ ‹እንዴ ቴዲን እኮ እያሰሩት ነው?› ካላችሁ፣ እንዴ እስክንድርንም እኮ ከሰባቴ በላይ አስረውታል እላችኋለሁ፡፡ ‹የፈለገውን አቋም መያዝ፣ ማራመድ ወይም አለማራመድ አይችልም እንዴ?› ካላችሁ ግን እስማማለሁ ግን ባያስጀምረን ነበር፡፡ የምርጫ 97 ሰሞን ጥዑም ፖለቲካ ዘፍኖ ከዘፋኝነት ወደነፃ አውጪነት ካሸጋገርነው በኋላ ማፈግፈጉ ያኔ የሕዝቡን ትኩሳት ተንተርሶ ሊጠቀምብን ነበር ማለት ነው? ያኔ ተቃዋሚዎች ተስፋ አላቸው ከነርሱ ልወዳጅ ብሎ ነበር ማለት ነው? ዛሬ ድንገት ተነስቶ ‹የለም! ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ነገር አላየሁም፣ አልሰማሁም› ቢል እኔም አልሰማውም፡፡

all of the reasons are also why i didnt bought the CD. thank God someone wrote about it. i thought it was only me. good job
የስነ ፅሁፍም የአስተያየትም ሃሳብን በቀጥታ የመግለጽም ብቃት የሌለው ፅሁፍ ሳይ ይህ የመጀምሪያዬ አይደለም ብዙ ብዙ በታዋቂ ሰዎችና ፍቅር ሰላም አንድነትን በሚያዜሙ አርቲስቶች ላይ እንደአንተ አይነቶች አነሳ ሀያሲያን ሲተቹ አጋጥመውኛል፡፡በዚህ በተወላገደ ብዕርህ ስለ ጠቅላይ ሚንስትርህ ቅንድብ የዘፈነውን እያሞገስክ ፅፈህ ቢሆን ኖሮ አበጀህ ያሰኝ ነበር በአንጻራዊነት የአእምሮ ተመጣጣኝነት ስለሚታይበት ነገር ግን የምቀኝነት፡ የፍቅርና የአንድነት መንፈስ እጥረት በሽታ ያለባቸው ሰዎች የሚያሳዩት በህርይ ስለሆነ ቶሎ ብለህ የአእምሮ ሃኪም እንዲያይህ ብታደርግ መልካም ነው፡፡
MakeSense Ato በፍቃዱ ዘ ኃይሉ!!!
አማርኛ የኢትዮፕያዊነት መገለጫ ያደረገው ማነው??????????????????????????????????
እዉነት ብለሃል ጥሩ ተመልክተሃል!
Hey man, Get Life!!!
Stop talking rubbish and cheap!!!
Do something better and show us your intelligence in your area of specialty!!!!
Teddy is always there and He is in what he uses to be. He has been the peoples’ baby and He is always!!! His current release is the same as those what he gave us before. He deeply advocates Unity, togetherness and Freedom!!! Where is the flaw he had????
You are a confused coward and cheap monger with a blind political and trash ideology!!!
You didn’t do anything important as equal as what Teddy has done but you are there to discredit, badmouthing, mudslinging, defamation & character assassination.
Don’t Talk Cheap, Man!!!!! Get Life!!! hateful Trash!!!
Do you count yourself as blogger? I feel ashamed of you.
ምን አገባን መብትህ ነው ቴዲም ቢሆን ለራሱ ነው
30 ብር ማለት በኢትዮጵያ ነውውውው? በዶላር ነውውው? በናቅፋ ነውውው? በዚምባብዌው Z$ ነውውው? እስኪ ብር የምታመሰጥሩ ባለቅኔዋች እስኪ ትርጛሜ ስጡን;;
ወያኔ ቴክኖሎጅን እንደ ጫት ብቸኛ አቅራቢ ቢሆን ኖሮ ብላችሁ አስቡት ይህ የቴዲ ካሴት በስኣት 30 ብር ይከራይ ነበር ይሆን? እኔ እንጃ :: ግን የሆነው ሆኖ ዘንድሮ የአዲስ አበባን የገብያ ውሎ የሚን
ነግረን ሰው የለም እንዴ? እረባካችሁ ለጠሎት እንኩአ እንዲረዳን መረጃ አሻግሩልን:: አቤ ቶክቻው ታከተሽ እንዴ ኪይቦርድ መተክተኩን? እያዋዛሽ በነገር ጎንተል አድርጊው እንጂ(እምቢ ካልክ እቲቭኢ እንዳልከፍት ዋ!)
የቴዲ ካሴት እንደ ዶሮ ዋጋ የክፉ ዘመን ማስታወሻ ይሆናል
“ያኔ ትዝ ይልሀል ዶሮ እንኻን በአቅምዋ ብር 249.99 ቴዲ እንኻን ያለአቓሞአ ብር 29.99 ” ይጠይቁን ነበር
ትርጉም
ሁልት ሰው በትክክል የማታጠግብዋ ያች ኮስማና ዶሮ አቅም ሳይኖራት:….
ቴዲ በድሮ ጥንካሬዋ የጸና አላማዋ ብሄራዊ መዝሙር ታዘምረን እንዳልነበር አቆአሞአን ገልብጣ….
This guy has a nice voice, but he was wrong when he joined the shallow Ahmara politics that can not get him anywhere. He can use his talent to teach and preach about peace like Ali Birra is doing. He serves his country better if he uses his art and talent to lead people towards love and peace. No reason to praise Hailesellasie or the እግረ ጠማማው አማራ.
This my view, what is yours?
ዝባዝንኪ ነዉ የጻፍከዉ!
አባ በ ማስታወቂያው ምናምን እስማማለሁ:: የፈለገ እንግሊዘኛ ሰዉ ቢለፈለፍም ገን እንደዚህ አይነትይ ጉዳዮች ላይ ዝም ብለው የሰለጠኑ እየመሰላቸው የሚሰሩት ሰራ በታም ያቃጥለኛል::ግን ዘፈኑን በመጀመሪያ በውስጥህ ከባድ የማዳመጥ ፍላጎት እና ከባድ ጉጉት ከሌለህ የዘፈኑን
ሰሜታዊ ትርጉም ለማግኘት የሚያስቸግር ዪመሰለኛል:: ታድያ ደሞ ለ ሰራው አዲስ የሆነ ግምት ወይም cradit መስጠት ነው እንጂ
ያለበሸ ከ እነ ያስተሰርያል ጋ ካወዳደርሽው የማይሆን ነገር ነው:: ያስተሰርያል እኮ በታም የተጋነነው በዛን ጊዤ የወያኔ ምርጫ ድራማ ነው እኮ!!! ግን ያም ሆነ ዪሄ አሪፍ ስራ ነው ብዬ እገምታለው:: ኦ ረሰቼ ሲዲው ደሞ የተወደደው በቂ ምክንያት አለው!!! አየሸ አንቺ ያሰብሸው ዝም ብሎ ርካሱ ሲዲ ላይ ማንም በ ቤቱ የሚቀዳበት ላይ የታተመ ይመስልሽ ይሆናል:: ግን አይሸ ኦሪጂናል ሲዲው የሚታተመው ጥራቱ በለጥ ባለ ዲስክ ሆኖ በብዛት ከ ህትመት ካምፓኒዎች ጋር በ መደራደር እና አብሮ ደግሞ የ አልበ ከቨሩ ከሲዲው ላይ ያለውም ስእል ጨምሮ ነው የሚታሰበው:: ደሞ በ እዚን ጊዚ አንድ ዶላር ከ 18 ወደ 20 የ ኢትዮጲያ ብር በሆነበት ዘመን ከሰራተኛው ደሞዝ: የ አታሚው አና አከፋፋዩ ትርፍ እና የ ሀትመት ንጥረ ነገሩ ጋር ፍጆታ ጋር ነው የጨመረው:: በ አጭር አማርኛ የኑሮ ውድነት ነው ማለት የምችል ይመስለኛል:: ግን ያ በተረፍ “ጥቁር ሰው” የምተባለው ዘፈኑ በ አድማጮች ላይ ብዙ ያለመስማማት ችግር እና ወከባ ያስመዘገበች መሆኑዋን በ እየ ዩቲዉቡ ድሬቲውቡ እና ኢትዮቲው ላይ ከቭኢዲዎች በታችህ ያሉትን አስተያየቶችህ እያየሁ በታም የሚገርሙ አና የሚያቃጥሉ ነገሮችህ እያነበብክ ነበር::
ያም ሆነ ይህ 7 አመት ከሙዚቃው ብዙም እርቆ የመጣን ዘፋኝ አሪፍ አልበም ነው ብዬ እደመደማለው::
በጣም የሚገርም ነው ምን ነካው ወያኔወ እኮ የሚያደርጉት አይታወቅም ታስሮ ከተፈታ ምናልባት ምናምን አስነክተውት ይሆናል አይታወቅም አስረው ሲፈቱ የሚያደርጉት አይታወቅም እግዝያብሕር የበፊቱን አላማ ይመልስለት
yeantem asteyayet(techet) betam yewrede new. plz try to analyse the right way if can’t please leave it for people who has knowledge for criticize
ሁልጊዜ የሚያስገርሙኝ እንዳተ ያሉት ነጻነት ፈላጊዎች በመሰረቱ ቡኬዎች፣በእራስ መተማመን ያነሳቸው፣በሰው መከራ፣ ስቃይ፣ሞት፣ የተደላደለ ኑሮና ነጻነት የሚሹ ናቸው። በዚህም ምክንያት እኔ ለወገኔ፣ለአገሬ ምናደረኩ?ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት ምን መዋጮ ከፈልኩ?ብሎ እራሳቸው ጥያቄ ከመጠየቅ ይልቅ፣ቴዲ አፍሮ እንዴት ስቃይና መከራው በወያኔ አዲቀጥትል መንገዱን አላመቻቸም የሚል የእቡይ ጥያቄ ያነሳሉ። ትላንትና ቴዲ አፍሮ በወያኔው የእስር ሲኦል የደረሰበተ ፍዳና መከራ እንደ ጅምር (ባይጀምረው ነበር!)ተቆጥሮ፣ሁለተኛና ሶስተኛውን የመከራ ድግስ ይጠብቃሉ።በጽሁፍ ዲሪቷቸው እንቶ ፈንቶ ይጭራሉ። “የምርጫ 97 ሰሞን ጥዑም ፖለቲካ ዘፍኖ ከዘፋኝነት ወደ ነፃ አውጪነት ካሸጋገርነው በኋላ ማፈግፈጉ ያኔ የሕዝቡን ትኩሳት ተንተርሶ ሊጠቀምብን ነበር ማለት ነው?” እንደዚህ ያለው ጥያቄ ነው ስመ ጸሐፊውን ባለ ዲሪቶ የሚያሰኘው።በመጀመሪያ ነጻ አውጪነት በሹመት የሚሰጥ አይደለም። ሀቀኛው ነጻ አውጪነት በፍጹም ለሀገርና ለወገን እራስን ለመስጠት ከእራስ ጋር ቃል ኪዳን መግባት ነው።ቴዲ አፍሮ በወያኔ ፍርድ ቤት ሰው በመኪና ገጭተህ ገለሃል ተብሎ በውሸት ሲከሰስ “ልጠቀምብን ነበር” ነው ማለት ክሱን ማቀነባበር ላይ ቴዲ አፍሮ ነበረበት እንደማለት አይሆንም??
ይሄነው ታሪክ ክለሳ። ያላዋቂ ሳሚ ምን ይለቀልቃል አሉ አበው።በፈቃዱ በመጀመሪያ የጠፋውን አንትነትህን ፈልግ።ከዚያም ለመስዋእትነት ትበቃ አትበቃ እራስህን ጠይቅ።ረዥም ጉዞ የሚጀመረው በአንደኛው እርምጃ ነውና ወደፊት።ያንንም ካልፈለክ ከዜሮ ጀምረህ ባለበት ሂድ።ወደ ቴዲ አፍሮ ከጥቆማው በፊት? የእራስህን ኃላፊነት ተወጥተሃል?????
ቴዲ አፍሮ አኛን አነሣስተህ አንተ ወደየት ገሸሸ ታስረህ ስትፈታ እንደልደቱ ለአንተም የዘመኑን ሀመር ገዝተው ጉቦ ሰጡህ እንዴ ወያኔ እኮ ሲሠርቅና ሲያሠርቅ ማንም አይችለውም
በውነቱ ጥሩ ነው እንኳን ለአልበም አበቃህ የፒኮክ ፍቅረኛ ምነው ኢትዮጵያዊነትን እየረሣህ መጣህ አንተ እኮ ጀግናችን ነበርክ አሁንም ጠንክር በርታ
so rubbish
ይሄን ፅሁፍ የፃፈው ምቀኛ የቀን ጅብ ነው !
We Ethiopians are reaching to a point dismantling each other!! So what do you expect from such weyanne commentator,do you know that Teddy is from gonder, Amhara.
ዕረቅናት ዕረቅናት
If you have any tallent, use it to build and not to destroy. Of course you have no power to destroy anthing but still use your time on this earth doing something meaningful. Tera alubalta yetem ayadersen.
teddy get his red card from lots of peoples and he will face that ugly situation soon.
adiss nigus enji lewt meche meta
was very hot at that moment but now he keep quite because they f*&ked him in kality
የሚገርመው…ይሀ አርቲስት ማለት የሚፈልገውን ማለት ይችላል:: ነገር ግን ትላንትን ዛሬ ለማድረግ መፈለጉ አና የትላንትን የታሪክ ስህተት አንደ ገድል መዝፈኑ ጥቂት የትላንት ናፋቂዎችን ከማስደሰት ያለፈ ምንም ስነጥበባዊ ፋይዳ አያስገኝለትም:: የኢትዮጵያ ጀግኖች እንደሆኑ ላንዱ ኢትዮጵያዊ ወዳጅ ለሌላው ጠላት ወይም ላንዱ መሪ ሌላውን አስመራሪ ናቸው:: ምናለ የዘመኑን እውነታ ዘፍኖ…አዳዲስ ብሔራዊ ጀግኖች እንዲፈጠሩ ቢያግዝ ወይ ቢረዳ? ታሪካችንን ጠለቅ ብሎ/አድርጎ ቢያነብ ደስ ይለኛል:: ለማንኛውም ጥበብ ለንጀራ ሳትሆን ለጥበብነት ብቻ የምትውልበትን ቀን እናፍቃለሁ….
You are too quick for critic. Try take at least to listen the music before sending a pre-written critic. If write an article on April 15, 3:00 A.M regarding to the whole album, you are not credible, but I respect your opinion. Most of you evluation criteria does not persude Elia’s critical readers
Befkadu, Don’t touch Teddy! Don’t mention his name in a bad way! Are you trying to make him look bad in our eyes? That won’t happen. Teddy is loved and he is a true Ethiopian. Anyways, why don’t you tell him your concerns in private if you really love him?? You call yourself Ethiopian?? or Woyane sympathizer?? Which are you??
I wish all discussions would be in Amharic so we can experess ourselves better.
Everyone, please use Amharic fonts, encourage your kids to learn Amharic, it’s very important. I hope I am not digresing from the subject, but I saw one idiot’s comment that said “who says Amharic is an expression of being Ethiopia” Yes, you idiot, it is, you didn’t know that?? Well come to Ethiopia, our language is called Amharic, you will learn it, or you will perish. Wededkim telahim::
አያ በፍቃዱ ዘ-ኃይሉ
የቴዲን አልበም “ጥቁሩ ሰው”ን ያለመግዛት መብት አለህ::እኔ ደግሞ ለመውደድ መብት አለኝና በሥነ-ግጥም አወደስኩት እነሆ::
*******ጥቁር ሰው እንደዶሮ::*******
የፋሲካ በዓል ቢመጣ ዘንድሮ:-
በቴዲ ታረደ
ጥቁር ሰው እንደዶሮ::
አወይ መሞት ኖሮ:-
አይበስልም ወይ አሮ???
እርር ብሎ ከስሎ:-
የበሰለ መስሎ:-
በሕዝብ ደም ተማስሎ:-
ባጥንት ተቀቅሎ:-
በምንሊክ ምጣድ ቢራገብ ዘንድሮ{-
በካሴት ታረደ
ጥቁር ሰው እንደዶሮ::
ለነጻነት ችቦ በኤሎሄ ትንሳኤ:-
ለኢትዮጵያ ተስፋ ለሕዝቧ ሱባኤ
በሙዚቃ ቅላጼው ታሪክ ሊያመላክት:-
በእስር በወከባ በፍቅር ሲዋትት:-
አመታት ሲያስቆጥር ፋሲካን ዘንድሮ:-
ቴዲ አረደልን
ጥቁር ሰው እንደዶሮ::
እንግዲህ ትንሳኤ ነጻነት የሚሻ:-
ትግል ጎራ ይግባ ይቃመስ ከጉርሻ::
አውቆ የተኛ ሰው ፍፁም አይነሳ:-
ሕሊናውን አልፎ ልቡ እስከሚበሳ::
እናም በፋሲካ መግደፊያው ዘንድሮ:-
በቴዲ ታረደ
ጥቁር ሰው እንደዶሮ::
በራሴ እይታ ጥቂት ስህተቶች አይቻለው ነገር ግን አልገዛም የሚያስብሉ አይደሉም:: ወንድሜ አንዴ ደግመህ ስማውና ይሄ ቢስተካከል ብትል አይሻልም::
ያልገዛህበት ምክንያት ምቀኛ ስለሆንክ ነው ::
I respect your opinion even though that I completely disagree with you. I really doubt if the person who wrote this article listened to the album. Regardless of that, the point is, if the majority of Ethiopians going to like it or not. From the views, comments and feedbacks in youtube as well as social media sites, it looks like that the new album is going to be very successful.
ባንተ ቤት አስተያየት ስጥተህል:: ደካማ ነህ:: ገና ብዙ ማንበብ ያስፈልግሃል:: የገለጽከው መሃይምነትህን ነው:
ህይ ቴዲ ጅግናችን ነው ወያን ለምን ደሙ ለምን ፈላ
But what type of people we have in this world. It is frustrating to read this article, I don’t know he write it.
Character assassination, creating doubt and smeering as well as sneering are typical of TPLF prpaganda section that have gone to absurdity these days. Though freedom of expression is respected on this great paragon of democracy, I mean Elias Kifle, I do feel the overwhelming sense of frustration when such hod ader fools fill this website with their foul aand filthy notions.
Woyanne has taken popping up with degrading our Ethiopianism belief and butchering our national heros and unity symbols of the past and the present to a new level.Their dogs can write worse comments and paint decadent images on our sacred and authentic personalities. We should focus on our goal and should not be diverted from it as Woyanne loves throwing bones now and then to deflect our attention. Tyranny always falls as the human spirit has never been defeated. The sad fact is dictators do not and cannot learn from reality and fact.
God bless Teddy and all patriots of Ethiopia!
It is wrong to say we like tedy because he disrespect the government or promote any ideology he is a singer he can say anything …
አቶ በፈካዱ ሲለ እሱ ከመቅደድህ በፊት ሲለ ራስህ ተመራመር
I’ve wasted 5 precious minutes of my life reading this rubbish. If you wanted to write any critique about Teddy’s work, you should rise above your bias and hate. The motive is political… “ስንተዋወቅ አለች ዝንጅሩ” and you are the fox under the skin of the sheep. Pity you, you attack people if they happen to be challenging for the things you believed in. I am telling you, Teddy is the king. You are cheap-ass-moron-political-affiliated-person. and keep talking while you are running out of such talking
ምንድነው ነገሩ ? እስቲ ሰለ እሱ ብቻ ወረ አይደብራችሁም ? ዘፋነ በቃ ? why you guys make him that much important ? why you like to make him topics of your crap ? leave him alone ? he is a singer ,that is it. Go get your own bussines and leave his ass alone !
የፈለከውን ስታራ ብትውል ቴዲን እንደሆነ የ ኢትዮፕያ ህዝብ ይወደዋል,,,,,,long live tedy afro
ቴዲ አፍሮ የዝፈነውም ለራሱ ነው ምን አገባችሁ ደደቦች
ከታየ
አይ የምቀኝ ነገር እረ ሌላ ነገር አወራ ቲደን ተወው
Shall I also write in Amharic? I agree with the one who said I wasted 5 precious minutes of mylife. I hope you won’t be offended as you know you have written nothing at all, because you only wanted someone who could preach your hate towards EPRDF. If you have the gut why don’t you settle in Ethiopia and face this government as Birtukan has done. I always wonder why people like you say you are fighting this government or anything, without even commenting on something useful. I felt so shameful for you after reading almost all what you have written. Please don’t mention Birtukan’s name on anything realted to your politics, as she is the only one from this generation who deserve respect from all Ethiopians. Teddy has sone what he thought is good, that is all. Don’t try to associate him to your politics. Let me tell you about Yasteserial, He has said what he thought was right. Those EPRDF supporters were not the only ones who misunderstood him, you the socalled oppositions of EPRDF has also misunderstood him because what he said was something that a healthy and wise man will say about/for a change. Regarding Kab dahilak, may be you haven’t lost anyone from your family or friends because this war between Ethiopia and Eritrea. So you wanted the song for your consumption but he was singing about something that thouched literally everyone in Ethiopia because we were people marred to one another. I had seen my neighbour and friend who had grown with me in Debrezeit being a prisoner of war from the Eritrean side. So please don’t associate him to your bulshit politics. He was singing what a sane person would love to see, peace and love. I miss my Eritrean friends. They were Ethiopians till this government comes and tells them they are Eritreans and has to vote for the independence of Eritrea.
So if you were thinking Teddy was singing to your politics you have missed him. The new album still talks about Ethiopians and their heros.
Thank God I would never read your blog. I couldn’t stop writting but I have to. Don’t give yourself the place you don’t deserve like associating your self with Birtukan and Teddy, who had faced the brutality of this government for telling what they felt and thought.
I think I also went to extreme. If you had to comment please comment only on the music and even the lyrics but out of your political views and wanting to listen what you needed.
Bel Chaw