በቦሌ ክፍለ ከተማ 38.6 ሚሊዮን ብር የሚገመት መሬት የሸጡ በእስራት ተቀጡ

(በጋዜጣው ሪፖርተር)

በቦሌ ክፍለ ከተማ በመሬት ልማት አስተዳደር ውስጥ በተለያዩ የሥራ ኃላፊነት ይሠሩ የነበሩ ኃላፊዎችና ግብረ አበሮቻቸው፣ በሰሚትና በሲኤምሲ አካባቢዎች ግምታቸው 38,577,452 ብር የሆነ 82,038 ካሬ ሜትር መሸጣቸው በመረጋገጡ ከአሥር እስከ ዘጠኝ ዓመታት በሚደርስ ጽኑ እስራት ተቀጡ፡፡