በደብረማርቆስ ከተማ አንድ ኢትዮጵያዊ ላይ ራሱን አቃጥሎ ሞተ

“ታጠቅ ህሉፍ የተባለ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ሰራተኛ በደረሰበት አስተዳደራዊ በደል በሰውነቱ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ በደብረ ማርቆስ ከተማ ውስጥ ራሱን አቃጥሎ መሞቱን” የዓይን እማኞች ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ፡፡ የአካባቢ ነዋሪዎች እንደሚሉት “በደብረማርቆስ ከተማ ልዩ ቦታው አብማ 04 ቀበሌ በአቶ ጫኔ ቤት ውስጥ ተከራይቶ ይኖር የነበረው ታጠቅ ህሉፍ ራሱን አቃጥሎ ገሏል” ብለዋል፡፡

በአካባቢው የነበሩ የዓይን ምስክሮች እንደሚሉት “ታጠቅ ህሉፍ መኖሪያ አካባቢው ሄዶ በልብሱ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ እሳት ከለኮሰ በኋላ ወደ መነሐሪያ አቅጣጫ እየተጓዘ ድምጹን ከፍ አድርጐ ይናገር ነበር” ሲሉ ክስተቱን ያብራራሉ፡፡ ሂደቱን የተከታተሉት እንደሚሉት “ምን ሆነህ ነው? ለምን ራስህን አቃጠልክ?” ብለው እሳቱን ሊያጠፉለት ሲሞክሩ “ልታድኑኝ አትሞክሩ፡፡ መሞት አለብኝ፡፡ የትግራይ ልጆች የታገሉት እንዲህ ዓይነት ሥርዓት እንዲመሠረት አልነበረም፡ ፡ በህይወት ኖሬ እንዲህ ያለ ሥርዓት ማየት አልፈልግም፡፡ በዚች አገር ዲሞክራሲና ነፃነት የለም፡፡ ሠርቶ መኖርም አልተቻለም፡፡ በደረሰብኝ ጥቃት ራሴን መግደል ስለአለብኝ ነው፡፡ ወደፊት ሁላችሁም ትሞታላችሁ፡፡” እያለ ይናገር ነበር ብለዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት “በደረሰብኝ ጥቃት ራሴን መስዋዕት አድርጌአለሁ፡፡ እያለ ድምጹን ከፍ አድርጐ እየተናገረ ሲሄድ ልብሱ ተቃጥሎ አልቆ ሥጋው እየተቆራረጠ ወደ እግሩ ሲወድቅ በአሰቃቂ ሁኔታ ይታይ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት አንድ ነጭ ቲዮታ መኪና መጥታ ከጫነቺው በኋላ በመከላከያ ወታደሮች ታጅቦ ወደ ደብረማርቆስ ከተማ ሆስፒታል ገብቷል፡፡

ሆስፒታል ከገባ በኋላ ከሚያክመው ሐኪም በስተቀር ማንም ሰው እንዳያገኘው ተደርጐ ለሁለት ቀን ሆስፒታሉ በመከላከያ ወታደሮች
ሲጠበቅ ቆይቶ በሦስተኛው ቀን ህይወቱ በማለፉ ወላጅ አባቱ ከትግራይ ተጠርተው አስከሬኑን ወስደዋል” ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

ስማቸው እንደይጠቀስ የፈለጉ የሥራ ባልደረቦቹ ነን የሚሉ ግለሰቦች እንደሚሉት “የደብረ ማርቆስ ሆስፒታል ከሞያው ዲስፕሊን ውጪ
አድርጓል፡፡ ይህውም አንደኛ ታጠቅ ህሉፍ ተቃጥሎ ሆስፒታል ሲገባ የህክምና ካርድ ሳይወጣለት እንዲታከም አድርገዋል፡፡ ጓደኞቹና ማንኛውም ሰው እንዳያየው ከልክለዋል፡፡ ህክምናው ከአቅማቸው በላይ ከሆነ እንኳን ሪፈር ማለት ነበረባቸው፡ ፡ የህክምና ውጤት ሲየጠቁ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም፡፡ በመሆኑም የገቡትን የክምና ቃል ኪዳን ያልጠበቁ፣ የሞያውን ሥነ ምግባር ያላከበሩ ስለሆነ በህግ መጠየቅ አለባቸው” ይላሉ፡፡

ድርጊቱ የተፈፀመው መቼ ነው? በማለት ለጠየቅናቸው ጥያቄ ሲመልሱ “ድርጊቱ የተፈጠመው ታህሳስ 4 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀኑ በ11 ሰዓት ሲሆን ወዲያውኑ ሆስፒታል ገብቶ ታህሣሥ 6 ቀን 2004 ዓ.ም ህይወቱ ሊያልፍ ችሎአል፡፡ ከዚያም አባቱ ተጠርተው አስከሬኑን ትግራይ ወስደው ቀብረውታል” በማለት ይመልሳሉ፡፡ እስከዛሬ ለምን ተደበቀ? ብለን ለጠየቅናቸው ጥያቄ ሲመልሱ “መረጃውን ማንም
እንዳያገኘው በአካባቢው ከባድ ማስጠንቀቂያ በመስጠቱ ሰው ሁሉ ዝም ማለትን መረጠ፡ ፡ በአካባቢው ዜጐች ሁሉ በሥጋት የሚኖሩበት
አካባቢ ነው፡፡ ሳል እንኳን ብትስል ትርጉም ሠጥተው ለከፍተኛ ችግር የሚያጋልጡ ኃላፊዎች ያለበት አካባቢ ነው፡፡” ሲሉ መልሰዋል፡፡
የደብረማርቆስ ሆስፒታል ኃላፊዎችን ስለ ጉዳዩ መረጃ እንዲሰጡን ብንጠይቅም “እኔን አይመለከትም፡፡ የደረሰኝ መረጃ የለም፡፡ እኔ ስለማላውቅ ሌላውን አነጋግሩ” እያሉ ከጉዳዩ በመሸሻቸው ዜናውን ከዚህ በተሸለ ለመዘገብ አልቻልንም፡፡

“ታጠቅ ህሉፍ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት መካኒክ ሹፌር ሲሆን ጠይም ወፈር ያለ የትግረኛ ቋንቋ ተናጋሪ የነበረ መሆኑ ታውቋል፡
፡ ታጠቅ ህሉፍ ከ27-32 ዓመት ዕድሜ የሚገመት የወጣት ጐልማሳ እንደሆነ፤ በተፈጥሮው ትክክለኛ ያልሆነ ነገር ሲመለከት ሁል ጊዜም የማይደግፍ የዘረኝነትና የቡድተኝነት ስሜት የማይንፀባረቅበት እንደነበረ” በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ፡፡

“ከዚህ አስተሳሰቡ በአብዛኛው ከኃላፊዎቹ ጋር ይጋጭ እንደነበርና፡፡ የአለቆቹን ውሳኔ ይቃወም ስለነበረ፡፡ በተለያየ ጊዜ አስተዳደራዊ ጥቃት
ይደረግበት ነበር” ሲሉ በቅሬታ ይገልጹታል፡፡