ወያኔ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ወታደራዊ ሥምሪት እያደረገ ነው
በቱኒዚያ የፈነዳውና ከሰሜን አፍሪካ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የተዛመተው ህዝባዊ አብዮት ያስደነገጠው ዘረኛው መለስ ዜናዊና ፋሽስት ግብረ አበሮቹ በአዲስ አበባ ታላላቅ መንገዶችና ጉራንጉር ሠፈሮች ሳይቀር ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የደህንነት፤ የፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት ሃይል ማሰማራታቸውን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ በላከው ሪፖርት አስታውቆአል።
የብሄር ብሄረሰቦች መብት ለመጀመሪያ ጊዜ በአገሪቱ እንዲከበር በማድረጌና ልማት እና እድገት በማምጣቴ ህዝብ 99.6 % በሆነ ድምጽ መርጦኛል የሚለው ወያኔ አገኘሁ ያለውን የህዝብ ድጋፍ ለግማሽ አመት እንኳን በወጉ ሳያጣጥም ሊነሳብኝ ይችላል ብሎ ስጋት ውስጥ የከተተውን ህዝባዊ አመጽ በሃይል ለመደፍጠጥ፣ የመናገሻ ከተማውን ትላልቅና ትናንሽ መንገዶች በሙሉ የጦር ሜዳ ይመስል በወታደር ሃይል አሳጥሮታል እንደዘጋቢያችን ሪፖርት።
በድህረ ምርጫ 97 የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ በጠመንጃ ሃይል የሚበትን አጋዚ የሚባል ቅልብ ሠራዊት በአዲሳ አበባ ዋና ዋና መንገዶች ላይ በማሰማራት ከ200 በላይ ንጹሃን ዜጎችን ያስጨፈጨፈው ወያኔ የአያሏን አገር አመሪካ ድጋፍ በማግኘት የሰራውን ወንጀል ለማድበስበስ ሲል ወደ ጎሬቤት ሱማሌ ገብቶ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሱማሌ ዘጎችን በገዛ አገራቸው አንደጨፈጨፈ ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለው ታዋቂው የሰብ አዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አጋልጦ ነበር።
ይህ በንዲህ እንዳለ ሰሞኑን ሊቢያ ውስጥ ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ በህዝባቸው የደረሰባቸውን ተቃውሞ ለመበተን ቅጥረኛ ገዳዮችን በገንዘብ አስመጥተው ሊቢያዊያንን ማስጨፍጨፋቸው የተዘገበ ሲሆን ጋዳፊ ቅጥረኛ ወታደሮችን ወደሃገራቸው ለማስገባት የተገደዱት የራሳቸውን ወታደሮች በመጠራጠራቸውና ትእዛዜን አይቀበሉም ከሚል ስጋት እንደሆን ታውቁአል ከዚሁ ጋር ተያይዞ አልጃዚራ የዜና አውታር በሊቢያዊያን ቁጥጥር ስር የዋሉ በርካታ ቅጥር ነፈሰ ገዳዮችን ከነፓስፖርታቸው ያሳየ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የበርካታ ኢትዮጵያዊያን ፓስፖርቶች ታይተዋል ቀደም ብሎ ኢትዮጵያን ሪቪው በመባል የሚታወቀው የመረጃ ድረገጽ ባወጣው ጽሁፍ ከነኝህ የሊቢያ መንግስት ቅጥር ገዳይ ወታደሮች ውስጥ ኢትዮጵያዊያን እንደሚገኙበት መግለጹ ይታወሳል::