‹‹ብርቱካን ሚደቅሳ አሁን የፓርቲ ሥራ ለመሥራት ብቃት የለኝም ብለዋል›› ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
በታምሩ ጽጌ
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ወደ ፓርቲያቸው ተመልሰው የዕለት ከዕለት ሥራቸውን ለማከናወን አሁን ብቃት እንደሌላቸው ለፓርቲው መግለጻቸውን፣ በቅርቡ ኢንጂነር ግዛቸው የተኩትና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡