የዝቋላ ተራራ አካባቢ ደን ቃጠሎ
በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙርያ ባለው ደን የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት ሲጠፋ ሲነሳ አሁንም ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረ ይገኛል። ቅዳሜ መጋቢት ስምንት ቀን ከቀኑ ስድስት ሰዓት አካባቢ ልዩ ስሙ አዱላበ ከሚባለው ከገዳሙ ደቡባዊ ምሥራቅ አቅጣጫ የተነሳው የደኑ ቃጠሎ በመነኮሳቱና ባካባቢው ምዕመናን ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም ቃጠሎው እስከትናንት አመሻሽ ድረስ ዘልቋል። ወኪላችን ታደሰ እንግዳው እንደዘገበው፡ የገዳሙ ባለቤትና ጠባቂ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ቤተክህነት ችግሩ እንዲወገድ አስፈላጊውን ርዳታ አላፈላለገም በሚል ምዕመናኑ ወቀሳ ሰንዝረዋል። ያዳምጡ