መሪዎች ከዓረብ አገሮች አብዮት ምን ይማራሉ?
በቱኒዚያ የተጀመረው የዓረብ አገሮች አብዮት ፕሬዚዳንት አል አቢዲን ቤን አሊን ለ23 ዓመት ከተቆናጠጡበት የሥልጣን ወንበራቸው አስነስቷቸዋል፡፡ አብዮቱ በግብፅ ቀጥሎ በታህሪር አደባባይ ለ18 ቀናት በተካሄደው ተቃውሞ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክን ለ30 ዓመታት ከተደላደሉበት የሥልጣን ወንበር አሰናብቷቸዋል፡፡ ይህ የዓረብ አገሮች አብዮት እንደ ወረርሽኝ በባህሬን፣ በየመን፣ በሊቢያ፣ በኢራንና በዮርዳኖስ የተዛመተ ሲሆን፣ በቀጣይም አብዮት ሊነሳበት የሚችል አገር ማን ነው? የሚለውንም ጥያቄ እየፈጠረ ነው፡፡ ለረጅም ዓመታት በሥልጣን ላይ የከረሙ የአፍሪካ መሪዎችስ ከዚህ አብዮት ምን ይማራሉ የሚለውን የዘካሪያስ ስንታየሁ ዘገባ ለመመልከት እዚህ ይጫኑ፡፡