የመለስ መንግስት በኦብነግ እንቅስቃሴ እንደተሸበረ ዊኪሊክስ አጋለጠ

Ethiopia Zare ረቡዕ የካቲት 9 ቀን 2003 .. Feb 17, 2011) በኦጋዴን አካባቢ የሚደረገው የአማጽያን እንቅስቃሴ ከሚጠበቀው በላይ መንግስትን እንዳስጨነቀው በቅርቡ ይፋ የሆነው የአሜሪካ ሚስጥራዊ ሪፖርት አጋለጠ። በአዲስ አበባ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ዶናልድ ያማሞቶ በኖቬምበር 2007 በሚስጢር ያስተላለፉትን ዲፕሎማቲክ መልእክት ከትላንት በስቲያ (ፌብረርዋሪ 16) ያፋ ያወጣው ዊክሊክስ የኦብነግ እንቅስቃሴ ለህልውናየ ከፍተና አደጋ ፈጥሯል በሚል የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መግባቱን አብራርቷል።