የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ደን በመንደድ ላይ ነው

ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የሚገኘው የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ደን በመንደድ ላይ መሆኑን የገዳሙ አባቶች እየተናገሩ ነው፡፡ እሳቱ መንደድ ከጀመረ ወደ ሃያ አራት ሰዓት ሊጠጋ ነው፡፡ መንግሥት ከአካባቢው የውኃ ቦቴዎችን እና ወታደሮችን በማንቀሳቀስ ውኃውን ለማጥፋት ጥረት እያደረገ ቢሆንም እሳቱ ግን ወደ ገዳሙ በመጠጋት ላይ ነው፡፡

አሁን አማራጫችን አንድ ብቻ ነው፡፡ የዝቋላን ገዳም ከማጣታችን በፊት ያለንን ነገር ሁሉ ይዘን በተገኘው ትራንስፖርት ወደ ዝቋላ መትመም ብቻ፡፡ ወንበር ማርያም ድረስ የውኃ ቦቴዎቹ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ያለውን ባገኘነው ዕቃ ሁሉ ውኃውን ይዘን በመውጣት መረባረብ፡፡ ያለበለዚያ ግን የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ወደ ታሪክነት ይቀየራል፡፡

እነሆ ክርስትናችን የሚፈተንበት፣ ኢትዮጵያዊነታችንም የሚለካበት ጊዜ መጣ፣ በእሳት ተቃጥለው ያቆዩትን ገዳም ከእሳት ማዳን ካልቻልን እንግዲህ የኛ መኖር ትርጉሙ ምንድን ነው?

መኪኖች ያሏችሁ አንቀሳቅሱ፣ ጉልበት ያላችሁ ተንቀሳቀሱ፣ ሌላም አማራጭ ያላችሁ በፍጥነት ተጓዙ፣እሳቱን በእምነት እንቅደመው፡፡