የኢትዮጲያዊት አለም ደቻሳ አሟሟት በቤይሩት
ይሩት ሊባኖስ ውስጥ የራስዋን ህይወት አጠፋች የተባለችው ኢትዮጵያዊት ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል ። በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል አቶ አሳምነው ደበሌ ትናንት ኢትዮጵያዊቷ የተኛችበት ሆስፒታል ሲሄዱ ህይወቷን እንዳጠፋች እንደተነገራቸው ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ። የኢትዮጵያዊቷን ጉዳይ የሚከታትሉ በዚያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ማሀበረሰብ እባላት ግን አሟሟቷ መታወቅ መጣራት አለበት ይላሉ ። ሁለቱን ወገኖች ያነጋገረው የጂዳው ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል። ያዳምጡ