የተስፋዬ ገብረአብ – ማስታወሻዎች

ነቀፋው፤ ስድቡና ምስጋናው ጋብ በማለቱ የተስፋዬን ሁለት ስራዎች (የጋዜጠኛውና የደራሲው ማስታውሻ) የተሰኙትን መጽሃፍት  ለማጣጣም ጊዜ በማግኘቴ ስለሁለቱም ያለኝን አስተያየት ባጭሩ ለመጎፈጫጨር ከዚህ በታች ያሉትን መስመሮች እጠቀማለሁ። ተስፋዬ የተዋጣለት ደራሲ ለመሆኑ ጠላቶቹ ሁሉ የሚቀበሉት እውነታ ስለሆነ የእኔ ምስክርነት አያስፈለገውም። የዚህ ጽሁፍ አላማም ምስክርነት ለመቆም አይደለም። የተስፋዬን ሁለቱን መጽሃፍት በሶስት ከፍዬ ለማየት እንጂ።

ሀ. የመጽሃፎቹ አጠራረዝ – ሁለቱም መጽሃፍት በመልካም ሁኔታ የተጠረዙ በመሆናቸው ገጻቸውን ለማገላበጥ ከመቅለሉም በላይ አልፎ አልፎ መጽሃፍትን ሳንብ እንደሚገጥመኝ ገጾች አፍትልከው አይወጡም። በዚህም የተነሳ ሃሳብን አሰባስቦ የመጽፍቶቹን መልእክት ለመከታተል ይቀላል – ማለፊያ ጥረዛ ነው።

ለ. የፊደላቱ አጣጣልና የአጻጻፍ ዜይቤው – በዘመኔ አያሌ መጽሃፍት አገላብጫለሁ። ግማሾቹ የመኖሪያ ብልሃት ፍለጋ የተከተቡ ሲሆኑ የቀሩት ደግሞ ለጊዜው ስርዓት ለማደር የተደበሉ ናቸው። አልፎ አልፎ በተባራሪ በእግራቸው የቆሙ መጽሃፍት ሲገኙ ደግሞ እስየው ያስበለኝ ነበር። አሁን እንሆ መኖሩን እንክዋን ሰምቼው የማላውቅ ተስፋዬ የሚባል ደራሲ መጽሃፍት አወጣ ሲባል በቀጥታ ሁለቱን መጽሃፍት በመግዛት በቅደም ተከተል አነበብኳዋቸው። አዝናንተው ያስተምራሉ። በተለይም የጋዜጠኛው ማስታውሻ ስብጥሩን የወያኔ የበረሃ ትግልና ከተሜ ከሆኑ ወዲህ ያላቸውን እኔ ብቻ የሚለውን ቅራሪ ህይወት አጉልቶ ያሳያል። ተስፋዬ ለሚያቀርባቸው ነጥቦችም እማኝ ስላከለበት ሲፈለግ የሚገኝ እውን ወሬ እንዳካፈለን ጥርጥር የለውም። በቀዝቃዛ ደም ሰውን መግደል ሙያ ብለው የያዙት ወያኔዎቹና ተለጣፊ ድርጅቶች እስከመቼ በሰው ደምና እንባ እየነገድ እንደሚኖሩ ባላውቅም ያለቅጥ የተጣመመና ሽፋፋ የፓለቲካ ዘይቤ እየተከተሉ እንደሆነ ህዝባችን ያውቀዋል። ጉራው፤ስድቡ፤ማስርና መግረፉ በቃ ሲለው ይቆማል። ጊዜ የማይገታው ግፍ የለምና! ሰብዓዊ ክብሩን ያጣ ትውልድ ሲነሳ ምንም ነገር አይገታውም። ያ ቀን ሩቅ አይሆንም። የተስፋዬም መጽሃፍ የሚያመላክተው ይህኑ የውስጥ ሽኩቻና የወያኔ ኢሰብዓዊነትን ነው። መቼ ይሆን ካለፈው ተምረን ለዛሬ በአዲስ ሃሳብ የምንቆመው። በጠራራ ፀሐይ ሰውን በግፍ መግደል፤ ማፈን፤ ሌብነት፤ውሽት፤ከዳተኛነት (ሃገርንና ወገንን)፤ የዘር ፓለቲካ አሳፍሮን የጋሪዮሽ አላማን የምንከተለው? በዘር የተሰመረ ፓለቲካ ለማንም አይበጅም። አሁን በሃገሪቱ ንዋይ እንዳሻቸው የሚዘንጡት የጊዜው ጌቶቻችን የአገሬ አዝማሪ

ያ ሁሉ መዝናናት ያ ሁሉ ደስታ

እልም ብሎ ጠፋ በነነ ባንድ አፍታ

እንዳለው ነው የሚሆነው። ወያኔ ዛሬን ተጠቅሞ ስብዕና የተሞላው ሁሉን ያቀፈ ለአንዲት ኢትዮጵያ ማለት እስካለቻለ ድረስ አወዳደቁ የከፋ ይሆናል።

ሐ. መጽሃፍቶቹ የሚያስተላልፉት መልእክት – ለእኔ ሁለቱም መጽሃፍት ተስማምተውኛል። መልዕክታቸው አንድ ባይሆንም ጥቅል ሃሳባቸው አንድነትን፤ የሃገር ፍቅርንና የህዝባችንን ሃበሳ (በውጭና በሃገር) ውስጥ ያመላክታሉ። ሰው በትላንት አይኖርምና ተስፋዬን በየምክናያቱ ከመወርፍ ይልቅ በርታ፤ አይዞህ ከጎንህ ተስልፈናል ብንለው ተፈጥሮ ከጊዜ ጋር ያደለውን ችሎታውን ለእኛ ጠቀሜታ የበለጠ እንዲያውለው ይገፋፋዋል። ስለሆነም ገምቢ ያልሆነ ብቅልና ጌሾ  ያጀበው ዘለፋችንን ተተን እስየው በርታ አይዞህ እንበለው። በሚቀጥለው መጽሃፍትህ እስካገኝህ ፈጣሪ ይጠብⷅህ።

አደፍርስ ተሰማ

36 Comments on “የተስፋዬ ገብረአብ – ማስታወሻዎች”

  1. የመጽሓፉ አላማ አላማ ሲገባህ ትረግመዋለህና አይዞህ ቀን ሁሉን ያወታዋል

    • የምንኖረው አምስቱ ህዋሳታችንን በመጠቀም ነው። ተስፋዬ በሁለቱ መጽሃፍት ያቀረበልንን ትረካ የግድ ተቀበል ያለህ የለም። ነፃ ነህ። እኔ ግን ከአሁኑ የገባኝ እንጂ ቆይቶ የሚገለጥልኝ ነገር የለም።

    • ፍርድ – እኔ የጠላ ቤት ወሬ ሰልችቶኛል። መረጃ ካለህ በማቅረብ ከደራሲ ተስፋዬ ጋር ተሟገት። ዝም ብለህ በነሲብ የምተለው ሁሉ ደንባራነት ነው።

    • የምትለው ድብቅ የተስፋዬ መጽሃፍ አላማ ሲገለጥልኝ ለቡና ጋብዥሃለሁ።

  2. Thank you Adefris!!
    These days it is difficult to have mature comment and discussion and comment on the web because of some TPLF/EPRDF paid hopeless diasporas who does not now any thing about history and the true nature of the ruling party.All they care is their benefit and the visible , loan and aid based building and road constructions while we are loosing our communal values which is core part for the survival of the society.I do not know how any reasonable mind would accept political,economic and military superiority of one part of the society in a mult-iethnic
    society.Do you ???

    • Your points are well taken. Ethiopia is run by a minority ethnic group bent to destroy the fabric of Ethiopianism.

    • It is hard to discern (distinguish) between evil and good. However, there is one thing we can do, that is to expose darkness with every resource and method we have.

  3. Tesfaye has done his best to divide Ethiopia along ethnic lines, particularly between the Oromos and the Amharas. I for one believe that genuine Ethiopians can do a lot better without any input from Tesfaye to forge our unity and conquor the intrigues of Isayias whom he serves.

    I am ashamed of you, Adefres Tessema.You are really a spoiler as your first name implies.

    • tulu Oda – People like you are no help; try to forgive and forget the past for the good of the country. Take a look of yourself in the mirror and see if you look the same as a year ago. People change. Things change. Get over it and be part of the solution than the problem.

    • Passing judgment on Tesfaye’s past is not the purpose of my article. I have no knowledge of his association with Shabia. Even if he does, it will not change my opinion of him as a writer.

    • ወዳጄ ሃይሌ
      የህይወት ስንክ ሳር በዝቶብኝ እንጂ መኖሩንስ አለሁ።

  4. You are as silly as a your comments. What have you done for the people of Ethiopia. Who said Tesfaye is with no fault? You are a pinhead with no cells in it.

  5. Tesfaye has done his best to divide Ethiopia along ethnic lines, particularly between the Oromos and the Amharas. I for one believe that genuine Ethiopians can do a lot better without any input from Tesfaye to forge our unity and conquor the intrigues of Isayias whom he serves.

    I am ashamed of you, Adefres Tessema.You are really a spoiler as your first name implies.

    • Perfect insight is better than perfect eyesight. Your 20/20 vision is no good. Life is a moving stream, your salty comment is a pile of trash. Move on…forget the past and focus on the future.

  6. አደፍርስ ተሰማ እንዲህ ይላል፡፡

    በዘመኔ አያሌ መጽሃፍት አገላብጫለሁ። ግማሾቹ የመኖሪያ ብልሃት ፍለጋ የተከተቡ ሲሆኑ የቀሩት ደግሞ ለጊዜው ስርዓት ለማደር የተደበሉ ናቸው።

    አቶ አድፍርስ፡ የቡርቃ ዝምታንስ አላነበቡትም ይሆን
    ያንን አንብበውት ከሆነ ከላይ የሰነዘሩት አስተያየት ተስፋየን የሚሳደብ ነው የሚሆነው፣

    • ውድ ጀማል – እኔ በትላንት መኖር ካቆምኩ ቆይቻለሁ። ሰውን አሁን በቆመበትና በሚያረገው ሁለንታዊ አስተዋጾ ማየት ይኖርብናል።

  7. ውድ ጀማል ምነው የተስፋየን መትሀፍ ጠላህው አትጠለአው ውደደው አስተማሪ

  8. ደራሲ ማለት ያየውን፣ የሰማውን፣ የዳሰሰውን፣ የቀመሰውን፣ ያሸተተውን በጥቅሉ በአምስቱ የስሜት ኅዋሳት የተረዳውን ነገር ሳይጨምር ሳይቀንስ በአጻጻፍ ቴክኒክ (ሥነጽሑፍ የምንለው እሱን ነው) አስውቦ የሚያቀርብ ጸሀፊ ነው። የተረዳውን ሳይጨምር ሳይቀንስ የራሱን አስተያየትና ፍርድ ፈጽሞ ሳይጨምርና ከማንም ሳይወግን እውነቱን ብቻ እንደወረደ የሚያቀርብ ማለት ነው። ደራሲ በፍጹም የሚከተለውን አይደለም። የርዕዮት ቀስቃሽ (ፕሮፖጋንዲስት) አይደለም – ፈጽሞ። በእውኑ ዓለም ግለሰቦች በእርሱ ላይ ያቀረቡትን ትችት በመጽሐፉ ዋና አካል (አንቀጽም ሆነ ምዕራፍ)ተጠቅሞ ስማቸውን በግልጽ እየጠቀሰም መልስ የሚሰጥም አይደለም – በፍጹም። መግቢያው ላይ አንዳንድ ነገር ማድረግ አልፎ አልፎ የተለመደ መሆኑ አይካድም። የመጽሐፍ ምዕራፍ ርዕሰጉዳይ ግለሰቦችን ማድረግ ግን ከደራሲነት የራቀ ነው። ሌላው ቀርቶ ማስተማር እና እውነተኛ ዜጠኞች እንደሚያደርጉት ማሳወቅ እንኳን የደራሲ ዓላማው አይደለም – ብዙዎች እንደሚከራከሩት። ይህ ማለት ግን ድርሰቶቹ አስተማሪና አሳዋቂ ሊሆኑ አይችሉም ማለት አይደለም – ሊሆኑ ይችላሉ። የርሱ ዓላማ ግን የተረዳውን እውነት አምጦ እንደመውለድ ዓይነትና አንዴ የፈጠራቸውን ገጸ-ባሕሪያት ሊቆጣጠራቸው በማይችል ሁኔታ የሚሆኑትን እየተከተል መክተብ እንጅ ሌላ አይደለም። ከአገራችን የአቶ ሀዲስ ዓለማየሁንና የበዓሉ ግርማን ድርሰቶች መመልከት በቂ ነው። እንግዲህ በዚህ መስፈርት ነው ተስፋየን መመዘን። ፍርዱን ለአንባቢ እተዋለሁ።

    • በእውነት ዓለምና በህልም አለም መኖር ታላቅ ልዪነት አለው። አንተ እንዳለምከው ነገር ሁሉ ቢሆን ኑሮ አለማችን የተለዬ ገጽታ ይኖራት ነበር። የጠቀስካቸውን አንጋፋ ደራሲያን አውቃቸዋለሁ። የተስፋዬን መጽሃፍት እንዳለ አላምጠህ ዋጥ ያለህ የለም።

  9. ውድ ጀማል
    በመጀመሪያ አስተያየትክ ያንድ ደደብ ተማሪ እንጂ የበሳል ሃሳብ ሰጭ አይደለምና እባክህን ዝም ብትል ይበጃል ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል ቂቂቂቂ

    • ውድ ከበደ
      አንተ ጀማልን እየተሳደብክ የራስህን ሥልጣኔ ማንፀባረቅህ ነው? አሁንስ ባላዋቂ የተሳመው ከንፈርህ ከነንፍጡ ታየኝ። አይገባም ተራ ስድብ!

  10. ውብ አጻጻፉንና ፍሰቱን ስናይ ማን እንደ ተስፋይ ብንል ምንም ሃሰት የለበትም፣ እኔም እየጣመኝ ነው አነበብኩት። ግን ወንድሜ አስተውለህ ብታነበው እያዋዛ ጊዜ ሰጥቶ ለመግደል በጠይብ የተቀመመ ጣፋጭ መርዝ ነው። መርዙ ሲገለጥልህ ይበልጥ ታደንቀዋለህ ።

    • ውድ ሃብታሙ
      መርዝ መርዝ የሚሆነው ስትጨልጠው ብቻ ነው። እንደምታውቀው የሚጣፍጥ ነገር ሁሉም ከሆድ አይቆይም። የሚበጀውን ከመጽሃፍቶቹ በመያዝ መርዝ ነው የምትለውን ነገር ሲገለጥልን አብረን ማርከሻውን እንፈልጋልን።

  11. አደፍርስ…እውነትም አደፍርስ…በመጀመሪያ እኔም የተስፋዬን ሁለት መጣህፍት አንብቤአለሁ።ወድጃቸዋለሁም።ግን ሰዎች ይቀየራሉ እያሉ እርስዎ እንቡዋ ከረዩ ሲሉ..ደራሲው ስዬ አብርሃና ነጋሶ ጊዳዳ አልተቀየሩም የውሸታቸውን ነው ያለውን እንዴት አልተቹትም?ምን ማስረጃ አቅረበልዎ?እርስዎ ተለውጫለሁ…ደራሲውንም ኣላውቀውም እያሉ በግልጥ ዋሽተዋልየሰጡት አስተ የት በሙሉ በደንብ እንደሚያውቁት ያሳብቃል።ጭፍን ከመውደድና መጥላት አሁንም ልቦናዎ ይብራ።ያኔ ተለውጫለሁ ብለው ይደስኩሩ…

    • ተስፋዬን ከሰዬና ነጋሶ ጋር ማወዳደር እንቁላልና በርቱካንን እንደማነጻጸር ይቆጠራል። እርስዎ የጠቀሱአቸው ግለሰቦች አጥፍተናል ሲሉ አልሰማሁም። ተስፋዬ ግን በየአጋጣሚው ያለፈው ሩጫው የድንበር ገተር እንደነበርና ይቅርታም መጠየቁን አውቃለሁ። ሰዬ ወይም ነጋሶ በኢትዮጵያዊነታቸው ኮርተው ለአንዲት ሃገር እንቁም ሲሉ ተደምጠው አያውቁም። ይልቁንም የጎሳ ከለላቸውን ሲያጠናክሩ እንጂ።
      ለነገሩ የርስዎ ትችት ጅብ ከሄድ ውሻ ጮኼ እንዲሉ ነው። መራራ ከመሆን መልካሙን መርጠው የከፋውን አክእንትፍ ይበሉት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*