የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ በሐዋሳው ውዝግብ እና ለታላቁ የሚሌኒየም ግድብ ግንባታ ሥራ ስለሚደረገው አስተዋፅኦ ይወያያል


  • የሐዋሳው ችግር አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት ዝግጅት በአባላቱ የሐሳብ ልዩነት ሳቢያ  አልተጠናቀረም፤ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚያዘው አቋም ዋናው የልዩነቱ ነጥብ ነው።    
  • የአቡነ ጳውሎስ – አባ ሰረቀ ኮርፖሬሽን በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያወጀው የ‹ብጥብጥ አፋልጉኝ› እና የውንጀላ ዘመቻ ወደ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ቢዛመትም አሳፋሪ ገመናው እያደር በመጋለጥ ላይ ነው።
  • ከትላንትና ጀምሮ በኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ስም ‹‹ለሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ  ይቀርባል›› የተባለ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚከስ የአቤቱታ ፊርማ ተሰባስቧል፤ ለፊርማ  ማሰባሰቢያው ቅስቀሳ ላይ የዋለው ምፀታዊ ስልት ‹‹ያልፈረመ ተሐድሶ ነው›› የሚል ሲሆን ደቀ መዛሙርቱ አወጡት ከተባለው ባለአምስት ነጥብ የአቋም  መግለጫ አንዱ ደግሞ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን የታላቁን የሚሌኒየም ግድብ ግንባታን ይቃወማል›› የሚል እንደ ሆነ ተገልጧል። 
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት እና ገዳማት የአስተዳደር ሠራተኞች እና አገልጋዮች ለታላቁ የሚሌኒየም ግድብ ግንባታ የአንድ ወር ደመወዛቸውን  በዓመት ለማበርከት ወሰኑ፤ የአባ ሰረቀን ሰርጎ ገብ አጀንዳ ተቃውመዋል።
(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 13/2011)፦  ማክሰኞ ዕለት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ግፊት የተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ፡- በሲዳማ ጌዲኦ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በተፈጠረው የአስተዳደር ክፍተት፣ በሐዋሳ ሦስት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በተከሠተው አስተዳደራዊ ብልሽት እንዲሁም ይህን ተከትሎ በተባባሰው ሁከት እና ውዝግብ ላይ እንደሚወያይ የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች አመለከቱ፡፡

(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)