የመልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው አዲስ የጡመራ መድረክ


መልአከ ሰላም ደጀኔ ከልጃቸው ከዲ/ን አትናቴዎስ ጋር

(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 9/2010፤ ኅዳር 30/2003 ዓ.ም)፦ በግሩም ስብከታቸው እና በጠንካራ ጽሑፎቻቸው ለረዥም ዘመን ምእመናንን በማስተማራቸው የሚታወቁት መልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው ከመስከረም 25 ቀን 2003 ዓ.ም (ኦክቶበር 5/2010) ጀምሮ አዲስ የጡመራ መድረክ (ብሎግ) በመክፈት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። 

መልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው የሚያነሷቸው ርዕሰ ጉዳዮች በተለይም አሁን አሁን ከብዙ ሰባክያን አንደበት እና ከስብከት አደባባይ (ዐውደ ምሕረቶች) እየራቀ የመጣው የነገረ ሃይማኖት በተለይም የነገረ ቅዱሳን ጉዳይ በመሆኑ ደጀ ሰላማውያን በሙሉ እንዳያመልጣቸው ለማሳሰብ እንወዳለን።(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)