ሰበር ዜና፦ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆኑ
ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆኑ
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 28/2010፤ ጥቅምት 18/2003 ዓ.ም):- ቅ/ሲኖዶስ በዛሬ ከሰዓት ስብሰባው ለብዙ ጊዜ ሲያጨቃጭቅ በነበረው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ምርጫ ላይ በድምጽ ብልጫ ውሳኔ አስተላልፏል። ለቦታው ታጭተው ከነበሩት ሦስት አባቶች መካከል ማለትም ከብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ከብፁዕ አቡነ ያሬድ እና ከብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል መካከል ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስን በ22 ድምጽ መርጧል።የቤተ ክርስቲያን አምላክ የተመሰገነ ይሁን። አሜን።
ዝርዝሩን እንደፈፀምን እንመለስበታለን።
