“ ለጊዜው ተስማምተናል "

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 18/2010)፦
ክርስቲያን ተብለው የተጠሩ ሁሉ
ኧረ ምን ነካቸው አበዱ ይላሉ
ሞኞች ናቸው ጅሎች ቢዝነስ የማያውቁ
ያልኖረን ቃል ፈጥረው “ተጣሉ ታረቁ
ተወጋግዘው ነበር ዛሬ ግን ተስማሙ“
ብለው የሚያወሩ ሚያቦኩ የሚያሙ።
ድሮም አልተጣላን ክስም አልነበረን
በታክቲክ፡ነው፡እንጂ፡በዓላማ፡አንድ፡ነን::

እርግጥ በተሰለፍንበት ተመሳሳይ ሜዳ
በአጨዋወት ስልታችን አንዱ አንዱን ሲጎዳ
መኖሩን አንክድም ነበረን ተቃርኖ
ደጋፊም ተጣልቷል ሁለት ጎራ ሆኖ፡
አሁን ግን ተግባባን በጋራ ለመብላት
ለሰላም መግለጫም አቁመናል ሐውልት
ዓለም ባደነቀው በgive & take ስልት
እንደተሰጠን ስም – “ቅዱስ“ : “አቶ“ ሆነን
“ለእኔ“ “ለእኔ“ ክብር ልንሰራ ተስማማን
ወዮ ለእናንተ ውጪ ለቆማችሁ
ማልያ ቀይሮ መግባት ላልቻላችሁ
ለራሳችሁ አስቡ አንድ መልክ ላላችሁ
ዓለም ላይ ኖራችሁ “ዓለም“ ላልገባችሁ