የዘረኛው አምባገነን አገዛዝ ፓርላማ ምክር ቤት ተሰናባቾች የካድሬነት ስራቸውን ጀመሩ

ከተለያዩ ክልሎች በህዝብ ተመርጠናል ብለው በፓርላማ ምክር ቤት የቆዩት የዘረኛው ወያኔ አገዛዝ ሆድ አደሮች ከፓርላማ ምክር ቤት ከተሰናበቱ በሁአላ እዚያው አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች እንዲቀጠሩ ተደርገው የካድሬነትን ስራ እንዲያከናውኑ መመደባቸውን የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ በአስተላለፈልን ዘገባ ለመረዳት ችለናል:: እንደ ዘጋቢያችን ሪፖርት የቀድሞው የፓርላማ ምክር ቤት አባላት በአዲሶቹ ሆድ አደሮች ከተተኩ በሁአላ እንደ ማንኛውም የዘረኛው አገዛዝ ሆድ አደሮች አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የመሬት ቅርምትና ቤትም የመስራት ዘመቻቸውን አጡዋጡፈውታል::

በኢትዮጵያ ህዝብ ተከሻ ላይ ተፈናጦ የሚገኘው ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያዊያንን በዘር በሃይማኖትና በጎሳ ከመከፋፈል በተጨማሪ ለሆዳቸው ያደሩ ዜጎችን በጥቅም በመደለል በቀሪው ህዝብ ላይ የሚፈልገውን ተግባር ማስፈጸሚያ እያደረጋቸው እንደቆየ ይታወቃል::

የነኝህን የቀድሞ የፓርላማ ምክር ቤት አባላት ወደየ ክልሎቻቸው አለመመለስና በአዲስ አበባ ከተማ የካድሬነት ተግባር እየፈጸሙ ያሉ መሆናቸውን አስመልክቶ አስተያየት እንዲሰጡት ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው  የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ በሰጡት አስተያየት እንደተናገሩት እነኝህ ካድሬዎች ድሮውንም ቢሆን ወያኔ የመለመላቸው እንጂ ህዝብ የመረጣቸው አልነበሩም:: ፓርላማ በቆዩበት ጊዜም ቢሆን ሲያከናንውኑ የቆዩት ተግባአር እጂ ማውጣትና ማውረድ እንጂ ምንም ለሃገርም ሆነ ለህዝብ የሚጠቅም አልነበረም:: እንዲያውም በአጠቃላይ አገር የማጥፋት ተግባርን ነው ሲያከናውኑ የቆዩት:: አሁንም እዚሁ አዲስ አበባ ከተማ ተቀምጠው የካድሬነት ተግባር መፈጸማቸው አያስገርምም፣ ምክንያቱም ህሊናቸውን ሸጠው ለሆዳቸእው ያደሩ ናቸውና ብለዋል:: በመጨረሻም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ዘረኛው አምባገነን አገዛዝ እንደፈለገ እንድዲጨማለቅ ላደረጉት አስተዋጾ ዋጋቸውን የሚያገኙበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ቀናቸውን ነው የሚቆጥሩት በማለት አስተያየታቸውን አጠቃለዋል::