በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት 32 በመቶ ደረሰ፣ ዘረኛው የወያኔ አምባገነን አገዛዝ የሁለት አሃዝ እድገት ውሸትነት በድጋሚ ተረጋገጠ

ላለፉት ሰባት አመታት የሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት እንዳስመዘገበ፣ በአምስት አመቱ የልማትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተብየው ደግሞ ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ እያሰለፋት እንደሆነ፣ በቅርቡ ደግሞ የሚለኒየም ግድብ የተሠኘ የውሸት ፕሮጀክት ነጠላ ዜማ ይፋ ያደረገው የዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በየጊዜው እየጨመረ የሚሄደውን የዋጋ ግሽበት መቋቋም ተስኖት፣ በሃገሪቱ ያለው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በራሱ በወያኔ አፍ 32 በመቶ መድረሱ መታወቁን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ሪፖርት ገለጸ፣፣ እንደ ሪፖርተራችን ዘገባ የዋጋ ግሽበቱ በአንድ ወር ጊዜ ብቻ የሰባት በመቶ ጭማሪ አሳይቶአል::

ይህንን የዋጋ ግሽበት ተከትሎ የዘረኛውና አምባገነኑ አገዛዝ እንደ ግል ሃብቱ ተቆጣጥሮ ውሸት በሚያሰራጭባቸው የዜና አውታሮቹ፣ ቀደም ብሎ በሃገሪቱ በተከታታይ እየታየ ያለው የዋጋ ንረት የተከሰተው ስግብግብ ነጋዴዎች እቃዎችን ስለሚያከማቹና ተገቢ ያልሆነ ዋጋ ስለሚጠይቁ ነው በማለት የዋጋ ተመን ማውጣቱና በርካታ ነጋዴዎችን ወደ እስር ቤት ማጎሩ የሚታወቅ ነው። ይሁን እንጂ የፖለቲካ ትርፍ እስካስገኘ ድረስ አንድን ጥፋት በባሰ ሌላ ጥፋት ማድበስበስ ልማዱ የሆነው የዘረኛው መለስ ዜናዊና የባሌቤቱ አዜብ መስፍን አገዛዝ፣ የዋጋ ማስተካከያ አድርጊያለሁና ከእንግዲህ ወዲያ የኑሮ ውድነት ላሳር ነው በማለት በሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሃን ለአንድ ወር ያህል ህዝብ እንዳላደናቆረ በፍጆታ ዕቃዎች ጨርሶውኑ ከገቢያ መጥፋት ባዶነቱ እንደተጋለጠና እርቃኑን እንደቀረ የአደባባይ ምስጥር ሆኖአል።

የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ በርካታ የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ኢኮኖሚው ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ገንዘብ በማተም እድገት እንደተገኘ ለማስመሰል ያደረገው ጥረት የዋጋ ንረቱንና የገንዘብ ግሽበትን እንዳስከተለ በተደጋጋሚ መግለጻቸው አይዘነጋም:: ባለሙያዎቹ ዘረኛው አገዛዝ ያወጣው የዋጋ ቁጥጥር ተመን ሊሰራ እንደማይችል እንዲያውም ችግሩን ይበልጥ ለማባባስ የእቃዎችን አቅርቦት እጂግ ሊቀንሰው እንደሚችል አስቀድሞው ተንብየው እንደነበረና በገሃዱ አለም እየሆነ ያለውም ይሄው ሃቅ መሆኑ እየታየ ነው።

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በርካታ ከተሞች ስኳርና ዘይትን ጨምሮ በርካታ የፍጆታ እቃዎች ከገበያ ላይ በመጥፋታቸው የተነሳ አገዛዙ በማከፋፈሉ ሥራ ውስጥ እንደገባና ተጨማሪ የፖለቲካ ድጋፍ ማግኛ ምንጭ እያደረገው እንዳለ፤ በስርጭቱ ላይ አገዛዙን ለሚደግፉ ሰዎች እየተደረገ ያለው መድልዎ ማሳየቱን ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ግለሰቦች አረጋግጠዋል።