የአውሮጳ ፓርላማ የኢትዮጵያን ጉዳይ አስመልክቶ ስብሰባ አደረገ

አለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂውማና ራይትስ ዎች በግርድፍ ትርጉሙ ”ነጻነት አልባው ልማት” :የርዳታ ገንዘብ አፈናን ለማጠናከር ሲውል  Development without Freedom; How aid underwrites repression in Ethiopia በሚል ርዕስ ያወጣውን ሪፖርት አስመልክቶ ሁለት የአውሮፓ ህብረት ኮሚቴዎች ማለትም “የሰብአዊ መብት ኮሚቴ እና የልማት ኮሚቴ” በእንግሊዜኛው አጠራር Sub commitee on Human Rights and Committee on Devlopment ) የተባሉት ኮሚቴዎች በጥምረት ያዘጋጁት ስብሰባ መጋቢት 5 ቀን 2003 አም በአውሮፓ ፓርላማ ውስጥ መካሄዱን የግንቦት 7 ዘጋቢ ከብራስልስ ቤልጅዬም በላከልን ዘጋባ ገለጸ ።

የቀድሞው የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን የልማት ኮሚሽነር የነበሩት ሚስተር ሉዊ ሚሼል እና በምርጫ 97 የአውሮፓ ምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የነበሩት ክብርት አና ጎሜዝ በተሳተፉበት በዚህ ስብሰባ ላይ ሂውማና ራይትስ ዎችን በመወከል ሚስተር ቤን ራወለንስ ባቀረቡት ሪፖርት የቻይናው ማኦይስት ፈለግ የሚከተለው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በ እርዳታ የሚያገኘውን ገንዘብ ለፖለቲካ ድጋፍ ማግኛ እንደሚጠቀምበት በተለይ ደግሞ በሰፍቲ ኔት ለታቀፉትና ምግብ ለሥራ ፕሮግራም ውስጥ ለሚሳተፉት ሁሉ ዋና መስፈርቱ ለወያኔ ፖለቲካ ታማኝነት ወይም አባልነት በመሆኑ ይህ የ እርዳታን ገንዘብ አለአግባብ ከመጠቀም አልፎ ከሰብ ዓዊ መብት ጥሰት ጋር የሚቆራኝ ነው ብለዋል። የወያኔ ባለስልጣኖች የምዕራብ ለጋሾችን ለማማለል ስለዲሞክራሲና ሰብአዊ መብት አያያዝ ወገንተኝነታቸውን በመግለጽ የማይታሙ በተግባር ግን ኮሚንስታዊ የስልጣን ማዕከላዊነት በመዘርጋት ከላይ እስከታች ቀበሌ ድረስ ያሉትን መዋቅሮች የሚቆጣጠሩ ኮሚንስት አምባገነኖች ናቸው ሲሉ ነቅፈዋል። የሂውማን ራይትስ ዎች ተመራማሪ የሆኑት ሚስተር ራወለንስን ላቀረቡት ሪፖርት ማስተባቢያ ያቀረበው በቅርቡ በቤልጅዬም የወያኔ ኤምባሲ አንደኛ ጸሃፊ ሆኖ የተመደበ ግለሰብ የሂውማን ራይትስ ሪፖርት ከበስተጀርባው የፖለቲካ አጀንዳ ያለው አክራሪ የሆኑትን የአገሪቱን ተቃዋሚዎች ጩሄት እንዳለ ተቀብሎ የሚያስተጋባና ወያኔ እያስመዘገበ ያለውን ዕድገት ለማሰናከል እርዳታ እንዳይሰጥ የሚከላከል ነው በማለት ከውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ተጽፎ የተላከውን 2 ገጽ ጽሁፍ በ7 ደቂቃ ንባብ አሰምቶአል።

የአውሮፓ ግብር ከፋዮችን ገንዘብ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለሚፈጽሙ አምባገነን የአፍሪካ አገር መሪዎች የሚደለድለው የአውሮፓ ኮሚሽን ተወካይ በበኩሉ በአድስ አበባ የሚገኙ የለጋሽ አገር ተዋካዮች ቡድን ሂውማን ራይትስ ዎች ያቀረበውን ክስ በማስርጃ ለማስደገፍ እንዳልተቻለ መግለጫ ማውጣታቸውን እንደአስረጂነት በመቆጠር፡ የምዕራቡ አለም በአመት 3 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ መስጠት ከመጀመሩ ከ15 አመት በፊት ለኢትዮጵያ ተረጂዎች በአመት እስከ 700 ሺ ቶን እህል ይለገስ እንደነበረ ገልጸው ያቁጥር ዛሬ ወደ 400ሺ ቶን ወርዶአል በማለት ወያኔ በ15 አመት ጊዜ ውስጥ  ከ700 ሺ ቶን እርዳታ ተቀባይነት ወደ 400 ሺ ቶን መውረዱን እንደመሻሻል ገልጸዋል። በአገራቸው የሞርጌጅ ዕዳ መክፈል ፋታ የነሳቸውና ኢትዮጵያን ወደ መሰለች አገር ተልከው በዘረፋና ሙሲና ከተጨማለቁት አምባገነኖች ጋር የሚተሻሹ የምዕራብ ተወካዮች ወያኔ የሚፈበርከውን የዕድገት ቁጥር ሲያስተጋቡ ከሰነበቱ ቦሃላ 45 ቢሊዪን የሚጠጋ ገንዘብ በዕርዳታ በተሰጠበት 15 አመት እድሜ የዕርዳታ ምግብ ለምን መቀበል እንዳሰፈለገ ከመጠየቅ ይልቅ በግማሽ ያህል እንኳን ያልቀነሰውን ቁጥር አድንቀው ሲናገሩ ማስተዋል ስብሰባውን ለመከታተል በአዳራሹ የተገኙትን  ኢትዮጵያዊያን አስገርሞአል።

የሂውማን ራይትስን ዎች ለማጣጣል ከአዲስ አበባ ተጽፎ የተላከው ደብዳቤ ፡ክብርት አና ጎመዝን  የኢትዮጵያን ህዝብ ብሶት በየሄዱበት ከማስተጋባት እንዲቆጠቡ ከአሁን “ቦኋላ የመንግሥታችን ትዕግስት ከጣራው በላይ ሂዶአልና ይጠንቀቁ ” ሲል አስጠንቅቆአል። ማስጠንቀቂያውን የሰሙ አንድ የፓርላማው አባል የኢትዮጵያን ህዝብ ማሸማቀቅ አንሶባችሁ የተከበሩትን እና የሚያደርጉትን ጠንቅቀው የሚያውቁትን የፓራላማችን አባልን ለማስጠንቀቅ መሞከራችሁ ድፍረት ብቻ ሳይሆን ጥጋብ ነው ካሉ ቦኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደቱኒዚያው ህዝብ ለመብቱ የሚነሳበት ቀን ከፊት ለፊታችሁ መሆኑን ልትገነዘቡት ይገባል በማለት የወያኔ መል ዕክት ለማስተላለፍ የመጡትን  ተላላኪዎች አስገንዘበዋል።