አዲስ በአዲስ አበባ ሳሪስ ሁለት ወጣቶች ተገድለውና ተጥለው ተገኙ

ዘረኛውና ግፈኛው የወያኔ አገዛዝ በቱኒዚያ ተቀጣጥሎና የሰሜን አፍሪቃ ሃገራትን አዳርሶ ወደምስራቁ ክፍል እየገሰገሰ ያለው ህዝባዊ ማእበል በፈጠረበት ጭንቀት ምክንያት የሚያደርገው ተግባር ሁሉ የ እብድ ስራ እየሆነ መምጣቱን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ በላከልን ሪፖርትት ገለጸ እንደ ዘጋቢያችን ሪፖርት በአዲስ አበባ ከተማ ሳሪስ ተብሎ በሚጠራው  አካባቢ ሁለት ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለውና አንደኛው ወጣት አይኖቹ እንዲወጡ ተደርጎ ድልድይ ስር ተጥለው መገኘታቸውን ተገልጾአል።  ወጣቶቹ ከመሞታቸው በፊት በቱኒዚያና በግብጽ ስለነበረው ህዝባዊ አመጽ በስፋት ይከታተሉ የነበሩ እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን ግድያውን የፈጸመው የወያኔው ዘረኛ አገዛዝ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር እንደሌላቸው አንድ ስማቸው እንድይገለጽ የፈለጉ የሳሪስ ነዋሪ ገልጸዋል።

ዘጋቢያችን የሙዋቾችን ትክክለኛ ማንነት ለማወቅ እየጣራ የሚገኝ ሲሆን በአካባቢው ከነበሩ አንዳንድ ግለሰቦች ባገኘው መረጃ መሰረት፣ ወጣቶቹ ከየቤቶቻቸው በታጣቂዎች ምሽት ላይ ተወስደው እንደነበርና፣ በጃቸው ይዘውት የነበረ የሞባይል ስልኮችና መታወቂያዎቻቸውም የተወሰዱ መሆኑ ታውቁአል::

በሌላ በኩል በተያያዘ ዜና በሰሜን አፍሪቃ ህዝባዊ አብዮት ከተቀጣጠለ ወዲህ እንቅልፍ አጥተው ያሉት የዘረኛው አምባገነን አገዛዝ ቡድን አባላት የሚይዙና የሚጨብጡትን እያጡ ከመምጣታቸው በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያዊያን ነጻ ከሆኑ የዜና አውታሮች መረጃዎችን እንዳያገኙ በተለያየ መንገድ መሰናክል እየፈጠሩ እንደሚገኙ ታውቁአል  ከዚሁ ጋር ተያይዦ ኢትዮጵያ ውስጥ አልጃዚራ የቴሌቪዥን ፕሮግራም በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ መታፈኑም ተሰምቱአል። አልጃዚራ የዜና አውታር የሰሜን አፍሪቃ ሃገራቱን አብዮት በስፋትና በቀጥታ በመዘገብ የዓለም ህዝብ በየሃገራቱ እየተካሄዱ ያሉ ኩነቶችን እንዲያውቅ ና እንዲከታተል ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።

ዘረኛው የወያኔ አምባገነን አገዛዝ እየወሰደ ያለውን የእብዶች አይነት ስራ በሚመለከት አስተያየታቸውን እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የፖለቲካ ተንታኝ በሰጡን አስተያየት አምባገነኖች መቆሚያ መቀመጫ የሚያሳጣቸው አጣብቂኝ ውስጥ እስኪገቡ ድረስ እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ መፍጨርጨራቸው እንደማያስገርማቸው ገልጸዋል አስከትለውም እንዲህ አይነት አምባገነኖች የዘረኘነት ባህሪ ያላቸው ከሆኑ ደግሞ የሚሰሩት ሁሉ ለማመን የሚያስቸግር ጥፋት መሆኑ አይቀሬ ነው እናም የወያኔው አገዛዝ አባላት እንዲህ አይነት ርምጃዎችን መውሰዳቸው ህዝቡ በፍርሃት ተሸማቆ አጎንብሶ እንዲገዛላቸው ከሚያስቡት ከንቱ ቅዠት የሚመነጭ ተግባር ነው ያም ሆነ ይህ፣ ሊማሩ ቢችሉ ኖሮ ጠንካራና የተረጋጉ ናቸው በሚባሉት ግብጽና ቱኒዚያ የደረሰ ህዝባዊ አመጽ እዚህ መድረሱ አይቀሬነቱን ተረድተው በጊዜ ቢያመልጡ ይሻላቸው ነበር አለዚያ ግን እንዲህ አይነት ግፍና ጭካኔ የተሰራበት ህዝብ እነሱን ምን ሊያደርግ እንደሚችል መተንበይ ከባድ አይደለም በማለት ስተያየታቸውን አጠቃለዋል። ዶ|ር መራራ ጉዲና በአንድ ወቅት የሚበላውን ያጣ ህዝብ መሪዎቹን ይበላል ብለው አገዛዙን ማስጠንቀቃቸው ይታወቃል።