ጎጠኛው የወያኔ ቡድን ዘረፋውን አጡዋጡፎታል፣ መሬት ችብቸባ ተጠናክሮ መቀጥሉ ታወቀ
ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ ቡድን ቁንጮዎች በግብር በመዋጮና ኑሮን በማስወደድ ከህዝብ ከፍተኛ ገንዘብ ሲዘርፉና በውጭ አገርም በሚገኙ ባንኮቻቸው ሲያከማቹ የቆዩ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህ አልበቃ ብሉአቸው ደሀውን ገበሬ ከመሬቱ በማፈናቀል ከፍተኛ ዶላር ለሚከፍሉዋቸው አምባገነን መሪዎችና ድርጅቶች መቸብቸባቸውን አጡዋጡፈው እንደቀጠሉ መሆኑን ዊኪ ሊክስ ባወጣው ሚስጢራዊ መረጃ አጋለጠ።
እንደመረጃው ከሆነ የቀድሞው የናይጄሪያ መሪ ኦሌሴንጎ ኦባሳንጆ እና የጅቡቲው መሪ እስማኤ ኡማር ጉሌህ ከአዲስ አበባ ውጭ ከፍተኛ መጠን ያለው መሬት በረዥም ሊዝ ለሆቴል ግንባታ በሚል ስም መውሰዳቸው ሲታወቅ ኡማር ጉሌህ ከዚህ ቀደምም 7400 ሄክታር መሬት በመውሰድና ስንዴ በማምረት ወደ ጅቡቲ መላክ መጀመሩን አጋልጦአል። አንድ በግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የሚመራ ቡድንም ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከፍተኘ ስፋት ያለው መሬት ለመግዛት ድርድር የደረጉ ሲሆን አግሪ ቪይ በመባል የሚታወቀው የደቡብ አፍሪካ ኢንቨስትመንት ድርጅት 3.5 የአሜሪካ ዶላር በመመደብ የፍራፍሬ ማማምረትና ጭማቂዎችን በማዘጋጀት ወደ አውሮፓ ሀገራት ገበያ ለመላክ መዘጋጀቱም ታውቆአል፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ቻድሀ የሚባለው የህንድ ኩባንያ የአዲስ አበባን ሁለት እጥፍ የሚሆን መሬት እንዲሰጠው ጥያቀ ያቀረበ ሲሆን እስካሁን 22 ሺህ ሄክታር መሬት የተሰጠው ሲሆን በቀጣይነትም የጠየቀው ክ100ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እንደሚሰጠው ቃል እንደተገባለት ለማወቅ ተችሎአል፡፤
ከዚህ ሁሉ መሬት የሚፈናቀለው ገበሬ ከብት እንኩዋን የማይገዛለት ገንዘብ እየተወረወለትና ከቦታው በግድ እየተፈናቀለ በገዛ አገሩ በየከተማዎቹ በስደት እንደሚሰቃይ የሚታወቅ ሲሆን በአካባቢው የቀረው ገበሬ ደግሞ በገዛ መሬቱ ላይ ለለት ጉርስ እንኩዋን በማትበቃ ገንዘብ እንዲያገለግልና ጉልበቱ እንዲበዘበዝ እየተደረገ መሆኑን በተለያየ ጊዜ መግለጻችን ይታወሳል።
ይህ ሁላችንንም በገዛ አገራችን ላይ የበይ ተመልካች ያደረገን መሆኑን የተናገሩ ሪፖርተራችን ያናገራቸው አንድ በአዲስ አበባ በጎዳና ላይ የሚኖሮ ተፈናቃይ ገበሬ በጣሊያንም ጊዜ እንዲህ አይነት ግፍ ያልደረሰ መሆንን አስታውሰው ከቤቴ ተፈናቅየ የሰው እጅ እያየሁ የምኖርበት ዘመን ላይ ከምደርስ ያኔውኑ በመልካሙ ጊዘ ሞቼ ቢሆን ይሻለኝ ነበር በማለት ሲቃ እየተናነቃቸው እንደነገሩት አስታውቆናል።