ዘረኛው መለስ ዜናዊ ኢሳት ከአየር ላይ የሚወርድበት ዕቅድ ተነድፎ እንዲቀርብለትአስቸኳይ መመሪያ አስተላለፈ
ላልፉት 20 አመታት በስታሊናዊ ጥብቅ የደህንነትና ወታደራዊ ሃይል ኢትዮጵያ አገራችንና ህዝቦቿን በጉልበት አፍኖ እየገዛ ያለው የመለስ ዜናዊና ጥቂት ግብረ አበሮቹ ቡድን ኢሳት የተባለው ነጻ የሚዲያ ተቋም የሚያስተላልፈው መረጃ ለሥልጣን ዕድሜው ስላሰጋው በአስቸኳይ የሚታፈንበት መንግድ ተጠንቶ እንዲቀርብለት ለጄለዎቹ ሰሞኑን ት ዕዛዝ ማስተላለፉን የግንቦት 7 መረጃ ምንጭ አስታወቀ።
እንደግንቦት 7 መረጃ ምንጭ መለስ ዜናዊ ይህንን ትዕዛዝ ያስተላለፈው የህወሃት አባል እና የአገሪቱ ኢንፎርሜሽን ቴክኒ ኦሎጂ ሚንስቴር በሆነው ገብረጽዮን ገብረሚካኤል ሰብሳቢነት ለሚመራው ፤ ከኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒከሽን ፤ ከሳይንስና ቴኪኒ ኦሎጂ፤ ከወታደራዊ ኢንጂኔሪንግ፤ ከመብራት ሃይል፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲት ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ዲፓርትመንት እና ለዚሁ ሥራ ተብሎ ከቻይና አገር ለመጡ የኤክስፕረቶች ቡድን ነው። ዜረኛውና ፋሺስቱ መለስ ዜናዊ መመሪያ አዘል ትዕዛዙን በሰጠበት ወቅት ” እጅግ የሰለጠነ ዘመናዊ መሣሪያ ከታጠቀ 10 ብርጌድ በላይ መንግሥታችንን ለማናጋት አቅም ያለውን ይህንን በምራባዊያን የተከፈተብንን የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ቴለቪዝን በምንም መነገድ ተሸክመን መኖር የለብንም ስለዚህም ገንዘብ ሊገዛው የሚችል ማንኛውም የቴኪኒ ኦሎጂ ዕውቀት፤ መሳሪያና የሰው ሃይል ተመድቦ ከሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ፡ከአየር እንዲወርድ መድረግ አለበት ፤ ለዚህ የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ወጪ አጥንታችሁ ከአንድ ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለኔ በቀጥታ ልታቀርቡልኝ ይገባል ” ማለቱ ታውቆአል።
ወያኔ ቀደም ሲል ኢሳትን ለማጥፋት አረብሳት በተባለው ካምፓኒ ባለሥልጣናት ላይ ከፍተኛ የሆነ ዲፕሎማቲክ ጫና ከመፍጠር አልፎ ከፍተኛ መጠን ያለው የአገሪቱን ሃብት በማፍሰስ ከቻይና የሳታላይት መጥለፊያ መሳሪያ አስገብቶ በሴሜን ተራራማ ቦታዎች ላይ እንደተከለ ከአረብ ሳት የተገኘው መረጃ እንደሚያረጋግጥ ኢሳት አስታውቆ እንደነበር አይዘነጋም ። ኢሳት ከአረብ ሳት ላይ ከወረደ ቦኋላ በታይኮምሳት በኩል የሚያስተላልፈው ስርጭት ተመሳሳይ በሆነ የወያኔ ጣልቃ ገብነት ለ24 ሰ ዓት ያህል ተቋርጦ እንደነበረና ወዲያውኑ የሳታላይት ካምፓኒ በመቀየር ወደ አየር እንደተመለሰ ይታወቃል። አድማጮቻችን የኢሳት ማኔጅመንት ቦርድ በዚህ መረጃ ላይ የሚሰጠውን አስተያየት ካለ በሚቀጥለው ፕሮግራማችን ይዘን ለመቅረብ እንደምንሞክር እንገልጻለን።