በአስመጪነት ንግድ የተሰማሩ ዜጎች ከወያኔ አባላት በሚደርስባቸው ህገ-ወጥ ውድድር እየተገፉ መሆኑ ታወቀ
ግብር የማይከፍሉ የወያኔ ባለስልጣናት እና ካድሬዎች ህግ አክብረው የሚሰሩ አስመጪ ነጋዴዎችን ከገበያው እየገፉ መሆናቸውን የግንቦት 7 ድምጽ ሪፖርተር ከአዲስ አበባ ዘግቧል።
በርካታ አስመጪ ነጋዴዎች ድርጅቶቻቸው አትራፊነታቸውን በማጣታቸው የንግድ ዘርፋቸውን ለመለወጥ እየተገደዱ ነው ያለው ዘጋቢ፤ እንዲከፍሉ የሚጠየቁት የግብር መጠን ሆን ብሎ ከመጠን ያለፈ ስለመሆኑ ምሬታቸውን እንዳሰሙት ገልጿል።
ለደህንነታቸው ሲሉ የድርጅቶቻቸው ስሞች እንዳይጠቀሱ የፈለጉት ነጋዴዎች፤ የገጠማቸው ችግር የፈተጠረው የተሰማሩበት ንግድ ተጠቃሚዎች አጥቶ ሳይሆን የገዢው ቡድን አባል የሆኑ ነጋዴዎች በዝቅተኛ ግብር ወይም በነጻ እያስመጡ በዝቅተኛ ዋጋ ለመሸጥ በመቻላቸው ነው ብለዋል። ይህ ሁኔታም ባሉበት የንግድ ዘርፍ ለመወዳደር እንዳላስቻላቸው እና ከገበያው መገፋታቸውን አስረድተዋል።