ከጥምረት ለነጻነት፣ ለእኩልነትና ለፍትህ በኢትዮጵያ (ጥምረት) መግለጫ

ጥምረት ለነጻነትለእኩልነትና ለፍትህ በኢትዮጵያ (ጥምረት) መግለጫ

ን መስከረም 24 2002 ዓ.ም

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ገጥሞት የነበርውን ስጠ – ድርጅት ፈተና በማሸነፍ፣ ድርጅታዊ አንድነቱን አጥብቆ መውጣቱ ለዘረኛው የወያኔ አገዛዝ መርዶ  ለኢትዮጵያ ህዝብ ደስታ ነው።

ባለፈው ምስከረም 17 ቀን 2003 ዓ.ም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በአሜሪካን ሃገር በዋሽንግተን ዲሲ ባካሄደው የምክክርና  የሽምግልና ስብስባ ድርጅቱን ሲያምሱት  የነበሩ ችግሮቹን በማቃለል ድርጅታዊ አንድነቱን አጥብቆ  በመውጣቱ ጥምረት ለነጻነት፣ ለእኩልነትና ለፍትህ በኢትዮጵያ የኦነግን አመራርና መላው አባላቱን እንኳን ደስ አላችሁ ይላል።

የኦነግ ውስጠ ድርጅት ችግር መቃለሉና ኦነግ እንደ አንድ ወጥ ድርጅት ተጠናክሮ መውጣቱ፣ የኦነግን መዳከምና መበታተን ሲመኝ ለነበረው ዘረኛው ወያኔ ቅስም ሰባሪ ኩነት እንደሚሆንበት ጥምረት በሚገባ ያውቃል። በኢትዮጵያ ውስጥ በዘረኛው የወያኔ አገዝዝ ምትክ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ምስረታ እውን እንዲሆን ኦነግ ሊጫወት የሚችለውን ቁልፍ ሚና ለሚያውቀው ወያኔ፣ ኦነግ ውስጣዊ ችግሩን አቃልሎ ፊቱን ሙሉ በሙሉ ወደ ዋናው የህዝብና የዴሞክራሲ ጸር ወደ ሆነው ወያኔ የሚያዞርበት ዋዜማ ላይ መገኘቱ ለወያኔ ትልቅ መርዶ ነው።

ይህ ለዘረኛዎቹ ወያኔዎች መርዶ ለህዝብ ወገኖች ግን ተሰፋን ሰንቆ  የመጣ የኦነግ ተሃድሶ፣  ዘረኛው የወያኔን ገዥ ቡድን  እያስለቀሰ ዲሞክራሲ ናፋቂ ወገኖችን እያስፈነደቀ እንዲቀጥል ኦነግ በውስጥ ችግሩ የተነሳ የባከኑበትን ውድ ጊዜዎች በሚያካክሱ አስቸኳይና አፋጣኘ ስራዎች ሊጠመድ እንደሚገባው የጥምረቱ ጽኑ እምነቱ ነው። ይህ አንገብጋቢ ስራ የዴሞክራሲ ሃይሎች በሙሉ በአንድነት ተባብረው በዘረኛው የወያኔ አገዝዝ ላይ የሚያቀጣጥሉት አምባገነን ዘራፊዎችን የማውደም ስራ መሆኑን ጥምረቱ ይረዳል።

ለዴሞክራሲ የሚታገሉ ሃይሎች ኦነግን ጨመሮ፣ ባንድነት ተባብረው የጸረ ወያኔን ትግሉን ይመራሉ ብሎ የኢትዮጵያ  ህዝብ በትግስት መጠበቅ ከጀመር ስንበቷል። የኦነግ የውስጥ ችግር መፈታት በሃገርና ከሃገር ውጭ የሚኖሩትን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ታላቅ ተስፋ  እንደዘራባቸው ይታወቃል። ይህንን ተሰፋ የሚመጥን ፈጣንና  ቀለጣፋ ምላሽ መስጠት በኦነግ ላይ ታሪክ የጣለበት ታላቅ አደራ መሆኑን ጥምረቱ ይገነዘባል። ኦነግ ይህን ታላቅ ታሪካዊና ህዝባዊ  አደራ ለመሸከም መወሰድ የሚግባቸውን ማናቸውንም ውሳኔዎች በድፍረት በመውሰድ በአጭር ግዚ ውስጥ የሚጠበቅበትን ከፍተኛ ሃላፊነት እንደሚሸከም ጥምረት ትልቅ ተሰፋ በኦነግ ላይ ጥሏል። ይህ ተስፋ ኦነግ ባስቸኳይ በሚወስደው እርምጃ  እውን ሊሆን እንደሚችልም ጥምረት ለነጻነት ለእኩልነትና ለፍትህ አንዳችም ጥርጣሬ የለውም።

ውድመት  በከፋፍለህ ግዛ ስልታቸው ህዝብን አናክሰው በስልጣን ለመቆየት ለሚመኙ የወያኔ ዘረኛ ገዥዎች !!

ድል ለዴሞክራሲና  ለነጻነት ሃይሎች!!

ጥምረት ለነጻነትለእኩልነትና ለፍትህ በኢትዮጵያ