ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ አወጣሁ ያለው የዋጋ ተመን የግብይት ቀውስ መፍጠሩ ተዘገበ

የወያኔው አምባገነን አገዛዝ የኑሮ ውድነትን ለመቁዋቁዋም በሚል ያወጣው የዋጋ ተመን ተግባራዊ ካለመሆን አልፎ አስፈላጊ የሚባሉ የምግብ ሸቀጦችን ሳይቀር ከገበያ ፈልጎ ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱን የ ቪ ኦ ኤው ዘጋቢ ፒተር ሃይላይን ገልጹአል፣ ፣ ፒተር በዘገባው የዋጋ ቁጥጥሩ በሃገሪቱ ግብይት ቀውስ መፍጠሩንና በሸማቺና የነጋዴው ማህበረሰብ ውጥረት ማስፈኑን በዚህም ምክንያት በርካታ ኢኮኖሚስቶችም የሁኔታውን አሳሳቢነት እያሳወቁ መሆናቸውን አክሎ ገልጹአል፣ ፣ እንደሃይላይን ዘገባ ባንዳንድ ቦታዎች ሸማቾች ከነጋዴዎች ጋር የተጣሉበትና የተጋጩበት ሁኔታም እንዳለ ታውቁአል::

በዘገባው ላይ አንድ ሸማች በሰጡት አስተያየት የወያኔው አምባገነን አገዛዝ ያወጣው የዋጋ ተመን ምንም የፈየደው ተግባር የለም፣ ፣ ቀደም ብለን መግዛት የምንፈልጋቸውን ሸቀጦች የመግዛት አቅም አልነበረንም፣ አሁን ደግሞ የሸቀጦች ዋጋ ቀንሱአል በመባሉ መግዛት የምንቺል ሲመስለን ተፈላጊዎቹ ሸቀጦች ገበያ ላይ ሊገኙ አልቻሉም ብለዋል::

የወያኔው አገዛዝ ባለፈው መስከረም በወሰደው የብር የምንዛሪ አቅም ማስተካከያ እርምጃ የዶላርን ምንዛሪ በ17 አሳደግሁ ካለ ወዲህ ከውጭ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የዋጋው መጠን በእጅጉ ማናሩ ይታወቃል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ የንግድ አለመመጣጠን ከፍተኛ እንደነበረና ወደ 5.8 ቢልዮን ዶላር የንግድ ጉድለት እንደተመዘገበ መዘገቡ ይታውቃል፡፡

ዘረኛው የወያኔአገዛዝ ከተመን በላይ ሲሸጡ የተገኙ ከመቶ በላይ ቸርቻሪዎችን ሱቆች መዝጋቱንና እንዲህ ዓይነት የዋጋ ተመን ጥሰቶች ከተደጋገሙ ጣት መቁረጥ እንደሚጀምር የአገዛዙ ቁንጮ መለስ ዜናዊ ማስታወቁ ይታወሳል::

ከዚህ ጋር በተያያዘ የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢኮኖሚስትና የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር አካል ዶር ታደሰ ብሩ የወያኔ የዋጋ ተመን ምንነት በሚል ለንባብ ባበቁት ጽሁፋቸው የኢትዮጵያ ህዝብ በከፋ ድህነት ውስጥ እየማቀቀ፤ ሰብዓዊ ክብሩና ነፃነቱ በዘረኞች ተነጥቆ ኑሮውን በባርነት እየገፋ ባለበት ባሁኑ ሰዓት “የዋጋ ማሻሻያ ኣደረግን” ብሎ ማወጅ አንድም የተቃውሞ ኃይልን ለመከፋፈልና የህዝብን ትግል ለማዳከም የሚደረገውን ደባ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ነጋዴን በህዝብ ጋር ለማጣላት ታቅዶ የተደረገ ስለመሆኑ ለኣፍታም መዘንጋት የለብንም ማለታቸው አይዘነጋም::