ብሩህ ራዕያችንን በተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደግፍ!
ደግ መመኘት መልካም ነገር ነው። የምፈልገውን ነገር ጠንቅቀን ማወቃችን እጅግ አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው። መድረሻችንን ማወቅ ያለብን ለጉዞ ከመነሳታችን በፊት ነው። አዎ! ግልጽ የሆነ ራዕይ ያለን መሆኑ ወሳኝ ነገር ነው።
ይሁን እንጂ ራዕይ ወሳኝ ነገር ቢሆንም እንኳን ብቻውን ግን የትም አያደርስም። ልንደርስ የምፈልገውን ቦታ ማወቃችን ጉዞው የሚፈልገውን ፈተና ለማሸነፍ እና ጉዞው የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ለመክፈል የሚያበቃ ብርታት ካልሰጠን ከንቱ ነው። መልካምን መመኘት፤ መልካምን ማለም ጥሩ ቢሆንም ምኞት በተግባራዊ እንቅስቃሴ ካልታገዘ ውጤታማ አይሆንም።
እንደባሮች አዋርዶ እየገዛን ያለው ዘረኛው የትግራይ ገዢ ጉጅሌ ተወግዶ ማየት የብዙ ኢትዮጵያዊያን ፍላጎት ነው ብለን እናምናለን። የዜጎች ነፃነት የተከበረባት፤ የህግ የበላይነት የነገሰባት፤ እኩልነት የሰፈነባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ማየት ብዙ ኢትዮጵያዊያን የሚጋሩት ራዕይ ነው ብለን እናምናለን። ችጋርና ድህነት ጠፍተው፤ የሌሎች አገሮች ተመፅዋችነታችን አብቅቶ፤ የህጻናትና የመሬት ሸያጭ ተወግዶ፤ በአረብ አገራት የእህቶቻችን የስቃይና ውርደት ኑሮ አብቅቶ ማየት ብዙዎቻችን የምንመኘው ነገር ነው ብለን እናምናለን። ባርነትንና ድህነትን ለመሸሽ ሲሰደዱ በበረሃ ንዳድ የሚያልቁ;፤ ባህር ውስጥ የሚሰምጡ እና በጎረቤት አገራት እስር ቤቶች ውስጥ የሚማቅቁ ዜጎች የሌሏት ኢትዮጵያዊያን ማየት ብዙዎቻችን የምንጋራው ራዕይ ነው ብለን እናምናለን።
እነዚህን መልካም ምኞቶች፤ እነዚህን ውብና ብሩህ ራዕዮችን የሚያሳካው ማነው? እንዴት ነው የሚሳኩት? መቼ ነው የሚሳኩት? እነዚህ መሠረታዊ ጥያቄዎች ናቸው። ለመልሱ ጣታችንን ሽቅብ ወደ ፈጣሪያችን ወይም ወደ ጎን ወደ ሌላው ወገናችን ከመቀሰራችን በፊት ራሳችንን እንፈትሽ።
ምኞታችን፣ ራዕያችን የሚጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኞች እስካልሆንን ድረስ መመኘታችን ብቻውን የትም አያደርሰንም። የኛ እልህ፤ የኛ የዓላማ ጽናት፤ የኛ ቁርጠኝነት የክፋት ኃይሎች ካላቸው ቁርጠኝነትና ጽናት በላይ እስካልሆነ ድረስ ሠናይ-ግብር ክፋትን ማሸነፍ አይቻለውም።
መልዕክታችን ግልጽ ነው። ፍትህን መናፈቅ፤ በዘረኝነት መንገሸገሽ፤ አምባገነን አገዛዝን አምርሮ መጥላት ጥሩ ነው፤ ግን በቂ አይደለም። በመሬት ላይ ያለውን ሃቅ የሚቀይረው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ብቻ ነው። እያንዳንዳችን በተቀናጀ መንገድ ትናንሽም ብትሆን ጠጠር ከወረወርን በአጭር ጊዜ ውስጥ ክፋትን ከአገራችን ማስወገድ እንችላለን።
ስለሆነም ለራስዎ፣ ለአገርዎ እና ለወደፊቱ ትውልድ ብሩህ ራዕይ ካለዎት እና ራዕይዎ ተሳክቶ ማየት የሚፈልጉ ከሆነ የሚከተሉትን ይፈጽሙ።
- የተደራጀ ትግል ባነሰ ወጪና በአጭር ጊዜ ውጤታማ ያደርጋልና ንቅናቄያችንን ይቀላቀሉ። የእርስዎን ዝግጁነት የሚመጥኑ የአደረጃጀት መዋቅሮችን፣ የትግል ስልቶችን እና የተሳትፎ ዓይነቶችን አዘጋጅተናል።
- በማናቸውም ምክንያት ከኛ የሚመርጡት፤ ከኛ በተሻለ የእርስዎን አገራዊ ራዕይ የሚያሳካ ሌላ ፀረ-ወያኔ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ካለ ይቀላቀሉት።
- ግንቦት 7ን እና/ወይም ሌሎች ፀረ-ወያኔ ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶችን በገንዘብዎ፣ በእውቀትዎና በጊዜዎ ይርዱ።
- ወያኔ እየሸረበልን ባለ የዘርና የሃይማኖት ቅራኔ ውስጥ እንዳንገባ፤ በኢትዮጵያዊያን መካከል መግባባት እንዲሰፍን ተግተው ይስሩ። በኢትዮጵያዊያን መካከል በዘርና ሃይማኖት ልዩነት ባለማድረግ አርዓያ ይሁኑ።
- በፀረ-ወያኔ ጎራ የተሰለፉ ኃይሎች ተባብረው እንዲቆሙ የበኩልዎን ድርሻ ያበርክቱ። የሌሎች ድርጅቶችን ህመምና ስጋት ለመረዳት ጥረት ያድርጉ። አስታራቂ ይሁኑ።
- ከአሉባልታ ነፅተው የተግባር ሰው ይሁኑ። ፓለቲካችንን ከውሸት፣ ከጭፍን ጥላቻ እና ተራ ወሬዎች ለማንፃት ተግተው ይስሩ።
- ከወያኔ ድርጅቶች ጋር ፈጽሞ አይነግዱ። እቃዎቻቸውን አይግዙ፤ አገልግሎቶቻቸውን አይጠቀሙ።
- በወያኔ ላይ ያለዎትን ተቃውሞ በተገኘው እድል ሁሉ ተጠቅመው ይግለፁ። ተቃውሞዎን በየበዓሉ፣ በየስብሰባው፣ በሩጫዎች፣ በሌሎች የስፖርት ዝግጅቶች ወቅት በጩኸት፣ በፉጨት፣ በየበሩና ግርግዳው በብጥስጣሽ ወረቀቶች በመፃፍ ይግለጹ። “ሞት ለዘረኛው ወያኔ!!! ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!!!” ይሁን መፈክርዎ።
- የህሊና እስረኞችን ይዘክሩ፤ ቤተሶቦቻቸውን ይደግፉ።
- የግንቦት7 ራድዮና ሳምንታዊ ጋዜጣን ይከታተሉ፤ ለሌሎችም ያሰራጩ። የሰሙትን መረጃ ወይም ዜና ሳይንቁ ለግንቦት 7 ይላኩ።
- በማናቸውም መንገድ ወያኔን የሚጠቅም ተግባር አይፈጽሙ። በመሬት ወይም በገንዘብ አይደለሉ። መለስ እያደለ ያለው መሬት የሱ አያቶች ከጣሊያን ጋር አብረው ሊያስወስዱት ሲጥሩ የእርስዎ አያቶች ደማቸውን አፍሰው ያሰረከቡን መሆኑን አይርሱ።
- የወያኔን የኢንቬስትመንት ግብዣ አይቀበሉ። የህዝብ መብት ባልተከበረበት፤ የህግ የበላይነት ባልሰፈነበት፤ ዘረኛነት በነገሰበት ሃገር ውስጥ ራስዎን የገዢው ሎሌ ካላደረጉ በስተቀር በጥረትዎ ያፈሩት ንብረት ባለመብት አለመሆንዎን ይወቁ። ሎሌ ከሆኑ ደግሞ ጊዜዓዊ ተጠቃሚ እንጂ ባለመብት አይደሉም።
- ውጭ አገር የሚኖሩ ከሆነ ለቤተሰቦችዎ ገንዘብ ሲልኩ የወያኔ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ማስታገሻ በማይሆን መንገድ ያድርጉት። ኦፊሲያላዊ መንገዶችንም ሆነ ወያኔ በየአገሩ ያደራጃቸው የገንዘብ ማስተላለፊያዎችን አይጠቀሙ።
- በአገር ቤት የሚገኙትን ወገኖቻችንን መረጃ ለማስራብ ወያኔ የሚያደርገውን የመገናኛ ብዙሃን አፈና ለመበጣጠስ ጥረት የሚያደረጉ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በገንዘብዎና በእውቀትዎ ይደግፉ::
- የዲፕሎማሲው ትግል አካል ይሁኑ። ሰላማዊ ሰልፍ ይውጡ፤ በረሃብ አድማዎች ይሳተፉ።
- ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የወያኔዎችን እኩይ ተግባራት ከማጋለጥ አይቦዝኑ። ለፓለቲከኞች፣ ለሕዝብ ተወካዮች፣ ለሥራ ባልደረቦችዎ፣ ለክፍል ጓደኞችዎ ዜግነትን ሳይመርጡ የወያኔን ዘረኝነት፣ ጨፍጫፊነት፣ ዘራፊነትና አምባገነንነት ያሳውቁ።
- ጠዋት “ዛሬ ለትግሉ የማበረክተው ምንድነው?” ብለው ይጠይቁ፤ ማታ ጠዋት ያሉዋቸውን ፈጽመው እንደሆነ ራስዎን ይፈትሹ።
ዘረኞችና አምባገነኖች ከጫኑብን ዜጋዊና ሃገራዊ ውርደት በአፋጣኝ መገላገግል የምንችለው እነሱ ሊያዋረዱን አምረውና ተግተው እንደሚሰሩ ሁሉ እኛም አምርረንና ተግተን “አትችሉም! አንፈቅድላችሁም!” በሚል እልህና ቁጭት በርትተን ስንሰራ ብቻ መሆኑን ፈጽሞ አይዘንጉ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!