በኢትዮጵያ ያለው የግብር አከፋፈል በዘር አድሎ ላይ የተመሰረተ ነው ተባለ

የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በኢትዮጵያ አገዛዝ የዘረጋው የግብር ስርአት በዘር አድሎ ላይ የተመሰረ ነው የሚሉ ዜጎች በአዲስ አበባ ለሚገኘው የግንቦት 7 ድምጽ ዘጋቢ ምሬት አሰምተዋል።

ግብር ለመክፈል ወደ ጉምሩክ ሄጄ ተሰልፌ ነበር ያሉት አንድ ግለሰብ፤ በወቅቱ አየሁት ስለሚሉት የአድሎ አሰራር አስረድተዋል። ከፊት ለፊታቸው የነበሩት ሴት 400 መቶ ብር እንዲከፍሉ ተወስኖባቸው ሳለ፤ ግብር ሰብሳቢዋ መታወቂያቸውን ካየችና በትግርኛ ካናገረቻቸው በኋላ ክፍያውን ወደ 4 ብር አውርዳ ሸኝታቸዋለች ብለዋል።

ተመሳሳይ መረጃዎችን ፍለጋ የተሰማራውን ዘጋቢያችንን ያናገሩ ግለሰቦች፥ ከወያኔ አገዛዝ ጋር የዘር ትስስር ያላቸው ሰዎች ንብረት የሆኑ አንዳንድ የንግድ ተቋማትን በመጥቀስ ግብር እንደማይከፍሉ ጥቆማ አድርገዋል።