የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እጥረት እንደቀጠለ ነው
በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደቀጠለ ያለው የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እጥረት ዜጎችን፣ በተለይም በንግድ የሚተዳደሩትን፣ ለእንግልት መዳረጉን ቀጥሏል።
በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ባለፈው ሳምንት በቀን እስከ ስድስት ሰዓታት ድረስ ባብዛኛው የመዲናይቱ ክፍሎች የኤሌክትሪክ ሃይል እጥረት እንደነበረ ዘጋቢያችን ያደረሰን መረጃ አመልክቷል። አንዳንድ አካባቢዎች ያለ መብራት ውለው ማደራቸውም ታውቋል። ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ የተለያዩ ክፍላተ ሃገራት፣ ያለ መብራት ውሎ ማደር እና መሰንበት የተለመደ ጉዳይ መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ።
የወያኔ አገዛዝ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ማስፋፋቱን ሽቦ የዘረጋባቸውን ከተማዎች በመቁጠር በየአመቱ ቢያስታውቅም፤ በነዚህ አካባቢዎች በቋሚነት የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት የሚያገኙ ከተሞች የሉም። ለምሳሌ ወያኔ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ የኤሌክትሪክ ሽቦ የተዘረጋባት አንዲት በምእራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ነዋሪ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት፣ መብራት ወደ ከተማይቱ ገባ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ በበጋ “የወንዝ ውሃ ቀነሰ”፤ በክረምት ደግሞ “ነፋሱ ምሰሶውን ጣለው” እየተባሉ በአመት ውስጥ መብራት የሚያገኙበት ጊዜ እጅግ በጣም የተወሰነ እንደሆነ ገልጸዋል። እኒሁ ነዋሪ ከጥቂት አመታት ወዲህ የኤሌክትሪክ ሃይል እጥረት መባባሱን እና መብራት ካሉባቸው ቀናት ይልቅ የሌለበት እንደሚበልጥ ተናግረዋል።
የወያኔ አገዛዝ ከውጭ የሚተላለፉ እንደ ቪ ኦ ኤ እና ኢሳት የመሳሰሉትን መገናኛ ብዙሃን ላይ አፈና ለማካሄድ ከፍተኛ መጠን ያለው የኤሌክትሪክ ሃይል እንደሚያባክን በተደጋጋሚ ዘግበን እንደነበር ይታወሳል። በሥራ ላይ የማይተረጎም ቃል መግባት የማይሰለቸው መለስ ዜናዊ ከ እንግዲህ በኢትዮጵያ ሻማ የሚፈለገው ለልዴት ቀን በ ዓል ብቻ ነው ባለ ጥቂት ቀናት ጀምሮ አዲስ አበባን በሚያክል አለም አቀፍ ከተማ ውስጥ መብራት በፈረቃ ጭምር የማይገኝባቸው ቀናት እየተበራከተ መምጣቱ የተለመደ ሆኖአል።