የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ያሉ ኤርትራውያን ስደተኞችን ለፖለቲካ ፍጆታ እየተጠቀመ ነው ተባለ

ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ኤርትራውያን ስደተኞችን አስመልክቶ ባወጣው መመሪያ ወደ 36 ሺ ይጠጋሉ ያላቸወን በፈለጉት ያገሪቱ ክፍሎች ተዘዋውረው መሥራትና መኖር ይችላሉ ማለቱ ብዙ ሰዎችን እያነጋገረ መሆኑን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ከስፍራው ከላከልን ዜና ለመረዳት ተችሎአል።

ከሁለቱም ወገን ወደ መቶ ሺ ለሚጠጋ የወንድማማቾች ህይወት ህልፈት ምክንያት በነበረው ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት “የዓይኑ ቀለም ያላማረንን ሁሉ የማባረር መብት አለን “ በሚል ፍጹም ዘረኛ አመለካከት ለ ዓመታት ያካበቱትን ሃብት ንብረት በህገ ወጥ መነገድ ዘርፎ ያባረረው ተመሳሳይ ዜግነት አላቸው የሚባሉትን ሰዎች እንደነበር የሚያስታውሱ ወገኖች ወያኔ ይህንን የሚያደርገው ለስልጣን ያበቃውን የአሁኑን የኤርትራ አስተዳደር ተቀናቃኞችን ለማበረታታት እንደሆነ ይናግራሉ።

የግንቦት 7 ድምጽ ዘጋቢ ያናገራቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፥ ኢትዮጵያውያን እራሳቸው እንደፈለጉ መንቀሳቀስ በማይችሉበት አገር ይህ መብት ለኤርትራውያን ተሰጠ መባሉ የማይመስልና ርካሽ የሆነ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ተብሎ የተቀነባበረ የተለመደው የወያኔ ቅጥፈት ነው ብለዋል። ወያኔ እንደ ኦሮሚያ ባሉ ክልሎች በሚገኙ አንዳንድ የኢትዮጵያ የገጠር መንደሮች በዘረጋው የቁጥጥር መዋቅር አማካኝነት፣ ገበሬዎች ከሚኖሩበት ቀጠና ውጪ ሲጓጓዙ ለካድሬዎች እንዲያስታውቁ እንደሚያስገድድ ይታወቃል።

በተያያዘ ዜና አንዳንድ ለዝግጅት ክፍላችን እየደረሱ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራውያን ስደተኞች ሥም የተለያየ ጥቅማ ጥቅም እየሰበሰበ እንደሆነ ተጋልጦአል። ለአገዛዙ ቅርበት ያላቸው አንዳንድ ምንጮች እንደምናገሩት የወያኔ ባለሥልጣናት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ በርካታ ሰላዮቹን ወደ ስደተኛ ካምፖቹ እያስገቡ ፣ ለኤርትራውያን ስደተኞች በሚሰጠው ዕድል ወደ ምእራብ አገሮች እንዲሄዱ በማድረግ ላይ መሆነቸውን የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ወያኔ ባለፈው ሳምንት ኤርትራውያን ስደተኞችን አስመልክቶ ባወጣው መመሪያ የተባበሩት መንገሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ተግባሩን እንደ ቅን በመቁጠር ለወያኔ መሪዎች ምስጋና ማቅረቡ ሌላኛው ወያኔ ከዚህ ርካሽ ተግባር ያገኘው ትርፍ ነው።