ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ሊቀላቀሉት ፈቃደኛ ባልሆኑ ዜጎች ላይ የጥቃት እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑ ታወቀ

ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ፣ “አንወይንም” ወይም ገዢውን ፓርቲ አንቀላቀልም ባሉ ዜጎች ላይ የበቀል እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ሰሞኑን ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰ ዘገባ አሳይቷል።

የግንቦት 7 ድምጽ ሪፖርተር ከአዲስ አበባ አጠናቅሮ እንደላከው ዘገባ፥ አገዛዙ እንዲቀላቀሉት ጫና ተደርጎባቸው ፈቃደኛ ያልሆኑ ሰዎችን በቁጥጥሩ ስር ያሉትን ፍርድ ቤቶች በመጠቀም ያለ በቂ ክስ እና ማስረጃ ወደ ዘብጥያ እያስወረወረ ነው።

በዚህ አኳኋን ሰሞኑን በደቡብ ክልል በአርባ ምንጭ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች የሆኑ አምስት ዜጎች የሁለት አመት እስራት በግፍ እንደተፈረደባቸው ሪፖርተራችን ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል። እንደ ምንጮቹ ዘገባ ግለሰቦቹ በማህበረሰባቸው ውስጥ ያላቸውን ተሰሚነት ለገዢው ፓርቲ ጥቅም እንዲያውሉ የወያኔ ካድሬዎች ሲያደርጉባቸው የቆዩትን ጫና አልቀበል ብለዋል።

ላለፉት አምስት አመታት የወያኔ አገዛዝ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን በጉቦ ወይም በማስፈራራት አባል ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል።