የአቡነ እስጢፋኖስ መኪና በድንጋይ ተደበደበ
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 4/2010):- ከአገልግሎት በመመለስ ላይ በነበሩት በጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ መኪና ላይ በተሰነዘረ የድንጋይ ውርወራ የመኪናቸው መስተዋት ሲረግፍ በእርሳቸውም ሆነ መኪናው ውስጥ በነበሩት በሌሎች ሰዎች ላይ ምንም አደጋ አለመድረሱ ታወቀ።
አደጋው የደረሰው ብፁዕነታቸው ሰኞ (26/11/2002) ከቀኑ 10፡00 ላይ ጦላይ ኪዳነ ምሕረት በነበረ ጉባኤ ላይ ቡራኬ ሰጥተው ወደ ጅማ ሲመለሱ መሆኑን እማኞች ገልፀዋል።
ከጅማ አዲስ አበባ መስመር ኦሞ ናዳ ወረዳ በደነባ እና አሰንዳቦ መካከል በምትገኝ ቦታ ላይ በተደራጀ ሁኔታ የብፁዕነታቸው መኪና ላይ አደጋ የጣሉት ሰዎች ከድንጋይ ውርወራ ባለፈ ሌላ ዓላማ ይኑራቸው አይኑራቸው ለጊዜው የታወቀ ነገር ባይኖርም ጉዳዩ ግን ለጅማ ፖሊስ ሪፖርት እንደተደረገ ተነግሯል።
በጅማ ከተማ የሚገኘው ሕዝበ ክርስቲያን ማክስኞ ከ8፡00-12፡00 ሰዓት ውይይት አድርጓል የተባለ ሲሆን ጉዳዩ በ1999 ዓ.ም በአካባቢው ከተፈጠረው የክርስቲያኖች ጭፍጨፋ አንጻር በቀላል እንዳልታየ ታውቋል፡፡
