መንግሥት የኦጋዴን የነዳጅ ይዞታዎችን እያጫረተ ነው

– ሰባት ኩባንያዎች የጨረታ ሰነድ ገዝተዋል

በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት በኦጋዴን ቤዚን ውስጥ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት የሚገኝባቸውን የካሉብና የሂላል መሬቶችን ጨምሮ፣ ፔትሮናስ በተሰኘው የማሌዥያ ኩባንያ ተይዘው የነበሩ የነዳጅ ይዞታዎችን የኢትዮጵያ መንግሥት በማጫረት ላይ እንደሆነ ታወቀ፡፡