የአያት አክሲዮን ማኅበር ተከሳሶች መከላከያ ምስክሮቻቸውን ማስማት ቀጥለዋል

– ፍርድ ቤቱ አንድ የመከላከያ ምስክርን እንዳይመሰክሩ አገዳቸው

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በመሠረተባቸው ክስ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት እንዲከላከሉ ብይን ያስተላለፈባቸው የአያት አክሲዮን ማኅበር ዋና ባለድርሻና ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ተሰማ፣ የፋይናንስና ኢንቨስትመንት ዳይሬክተር ዶ/ር መሐሪ መኮንንና የፋይናንስ ዋና ክፍል ኃላፊ አቶ ጌታቸው አጎናፍር ግንቦት 1 ቀን 2003 ዓ.ም ዘጠኝ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰሙ፡፡