የግል ድርጅቶች ጡረታ ፈንድ የፈጠረው ብዥታ
መንግሥት ያዘጋጀው የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ ረቂቅ አዋጅ ሰሞኑን ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ረቂቅ አዋጁ በፕሮቪደንት ፈንድ ታቅፈው ላልነበረ የግል ድርጅት ሠራተኞች ዋስትና እንደሚሰጥ የማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ይገልጻል፡፡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንዳንድ የግል ድርጅት ተቀጣሪዎች ረቂቅ አዋጁን በበጐ ጐኑ የተመለከቱት ሲሆን፣ የተወሰኑት ደግሞ በአዋጅ ላይ በተካተቱት አንዳንድ አንቀጾች ደስተኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የግል ድርጅት ሠራተኞች ላይ ብዥታን ፈጥረዋል፡፡