ኢትዮጵያና ኤርትራ፣ ጦርነት ወይም ሰላም?

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚገባቸው የጦርነት ቋንቋ ነው፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ ከ10 ዓመት በፊት በጠራራ ፀሐይ አሻፈረኝ ያሉትን የሰላም ሐሳብ በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ለነበሩት ኮፊ አናን እኩለ ሌሊት ላይ ከእንቅልፋቸው ቀስቅሰው ተንበርክከው እቀበላለሁ ባላሉ ነበር፡፡