የልማት ባንክ የቦንድ ገበያ ገጠር ላይ አነጣጥሯል

• በዚህ ዓመት መጨረሻ የተበላሸ ብድርን ወደ 9.7 በመቶ ዝቅ አደርጋለሁ አለ

በውድነህ ዘነበ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለማበደር ካቀደው 28 ቢሊዮን ብር ውስጥ 11 ቢሊዮኑን ከቦንድ ሽያጭ ለማግኘት ያለመ በመሆኑ፣ በጥልቀት ወደ ገጠር በመግባት ገበሬውንና የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን ሊቀሰቅስ ነው፡፡