የአዋሽ ባንክ ተከሳሾች ከአገር እንዳይወጡ እግድ ተጣለባቸው

– እያንዳንዳቸው በአሥር ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቁ

በታምሩ ፅጌ

የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበር ፕሬዚዳንት የነበሩትን አቶ ለይኩን ብርሃኑን ጨምሮ አሥሩም ተጠርጣሪዎች ከመጋቢት 28 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ከአገር እንዳይወጡ በፍርድ ቤት እግድ ተጣለባቸው፡፡