የአንድነት ፓርቲ የድርድር ሒደት ወደኋላ እየተጎተተ ነው

‹‹ሒደቱ በዚሁ ከቀጠለ ሽምግልናውን ለማቆም ወስኛለሁ››  የአስታራቂ ኮሚቴው ሊቀመንበር

በኃይሌ ሙሉ

በእነ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በሚመራው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲና በእነፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ቡድን መካከል በአስታራቂ ሽማግሌዎች አማካኝነት ሲካሄድ የቆየው ድርድር መቋጫ ከማግኘት ይልቅ፣ ወደኋላ እየተጎተተ መሆኑን የአስታራቂ ኮሚቴው ሊቀመንበር ለሪፖርተር ገለጹ፡፡